ቀደም ብለዉ የአሰልጣኛቸዉን ዉል ለአንድ አመት ያራዘሙት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ የነባር ተጫዋቾቻቸዉን ዉል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ።
በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ክለቡ ፋሲል ከተማ ሻምፒዮን እንዲሆን የድርሻውን የተወጣዉ እና በመከላከሉ ቀጠና ላይ ከቡድን አጋሩ ያሬድ ባየ ጋር በመሆን ምርጥ ጥምረትን ያስመለከተን ተከላከላዩ ከድር ኩሊባሊ ያለፋትን አራት አመታት ካሳለፈበት ከፋሲል ከነማ ጋር ለመቀጠል ፊርማዉን ማኖሩ ተሰምቷል።
ሌላኛው የኮንትራት ዉሉን ያደሰዉ ተጫዋች ደግሞ የሊጉ ኮከብ ግብ-ጠባቂ ተብሎ መመረጥ የቻለዉ ሚኬል ሳማኪ መሆኑ ተሰምቷል። 2010 ላይ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በወጥነት ክለቡን ሲያገለግል የነበረዉ ግብ ጠባቂዉ በቀጣዩ የዉድድር አመትም በአፄዎቹ ቤት እንደምንመለከተዉ እርግጥ ሁኗል።
እንደሚታወቀው ፋሲል ከነማ በቀጣዩ የዉድድር አመት ለሚጠብቀው የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎ እና በሊጉም የሻምፒዮንነት ክብራቸውን ለማስጠበቅ ይረዳቸዉ ዘንድ የተለያዩ ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸዉ መቀላቀል መጀመራቸዉ የሚታወስ ነዉ።
አስተያየት ይስጡ