መነሻ ገጽ ዜናዎች አፄዎቹ ከአመታት በኋላ ጠቅላላ ጉባኤን ያከናውናሉ
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከነማ

አፄዎቹ ከአመታት በኋላ ጠቅላላ ጉባኤን ያከናውናሉ

አጋራ
አጋራ

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች መልስ የሚያገኙበት እና ለውጦች የሚኖሩት ጠቅላላ ጉባኤ ዕሁድ ይከናወናል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በማደግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠንካራ ተፎካካሪ ከሆኑ ክለቦች ውስጥ መመደብ የቻለው እና የሊጉን ዋንጫም አንድ ጊዜ በማንሳት ስሙን በድል ዝርዝር ውስጥ ያስቀመጠው ፋሲል ከነማ ረዘም ካሉ አመታቶች በኋላ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳበት የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን ዕሁድ መጋቢት 13 ሊያከናውን መዘጋጀቱን የሀትሪክ ስፖርት መረጃ አመላክቷል።

የክለቡ ደጋፊዎች ክለቡ እየገጠመው ከመጣው የውጤት ማሽቆልቆል እንዲሁም ከተፎካካሪነት እየደበዘዘ መምጣቱን ተከትሎ በተደጋጋሚ ለውጦች እንዲመጡ በየአመቱ ተቃውሞን በማሰማት ፣ የአመራር ለውጥም ይደረግ እያሉ ድምፃቸውን ሲያሰሙ የነበረ ሲሆን በጎንደር ከተማ ከንቲባ እና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቻላቸው ዳኛው መልካም ፍቃድም በርካታ ጉዳዮች በሚነሱበት እና አዳዲስ ውሳኔዎች በሚወሰኑበት ጠቅላላ ጉባኤ የደጋፊው ተደጋጋሚ ቅሬታ ሊፈታ መሆኑን ጭምር በመረጃዎቻችን አረጋግጠናል። በጠቅላላ ጉባኤውም ክለቡ ዘለግ ላሉ አመታት ስራ አስኪያጅ ሆነው ክለቡን የመሩት እና ተደጋጋሚ ተቃውሞን ሲያስተናግዱ የሚታዩት አቶ አብዮት ብርሀኑን ጨምሮ እንዲሁም ክለቡን ለቀጣዮቹ አምስት አመታት በቦርድ አመራርነት የሚመሩ አካላትን የመምረጥ ሂደትም ጉባኤው እንደሚኖረውም ለማወቅ ችለናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...