መነሻ ገጽ ዜናዎች ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ሦስት ስመ ጥር አሰልጣኞች ሦስት ክለቦች ለማትረፍ በሀላፊነት ተረክበዋል

አጋራ
አጋራ

ላለመውረድ እየተጫወቱ የሚገኙ ሦስት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሦስት የሚታወቁ አሰልጣኞች ይመራሉ።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ስር የሚገኘው በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም በሁለት አጋጣሚዎች የተሳተፈው የመዲናይቱ ክለብ አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አመታት በከፍተኛ ሊጉ መሐል ሰፋሪ ሆኖ ሲጨርስ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ግን በሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በ13 ጨዋታ 8 ነጥብ ብቻ ሰብስቦ መጨረሻ ላይ በመቀመጥ ላለመውረድ እየታገለ ይገኛል። የቀድሞው የደደቢት አሰልጣኝ የነበረውን ኤልያስ ኢብራሂምን አሰናብቶ በምትኩ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ወደ ሰባት የሚደርሱ የከፍተኛ ሊግ ክለቦችን ያሰለጠነውን አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን ከትላንት በስቲያ የቀጠረ ሲሆን አሰልጣኙም በዚህ ሳምንት አራፊ በመሆኑ በቀጣይ ሳምንት ሀላባን የሚገጥሙ ይሆናል የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚመሩ ይሆናል።

ሌላኛው አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከርን ከሀላፊነት ያነሳው የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ተደልድሎ እየተወዳደረ የሚገኘው በደረጃ በሰንጠረዡ የመጨረሻው እና 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የሚገኙት ሐረር ከተማዎች አንጋፋውን የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፣ ባህርዳር ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና አዲስ አበባ ከተማ አሰልጣኝ የነበሩትን ጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎን) በቦታው ሾሞ ለከርሞ በሊጉ ለማቆየት የአሰልጣኙን ልምድ ፈልጎ ሾሟል።

ነቀምት ከተማም የቀድሞው አሰልጣኙን ትላንት መልሷል። የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ደቡብ ፓሊስ እና ሲዳማ ቡና ምክትል እና ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የመሩት እና በከፍተኛ ሊጉ በሀላባ እና እንዲሁም ነቀምት ከተማ አሰልጥነው ያለፉት አሰልጣኝ ቾንቤ ገብረህይወት በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ መጨረሻ ላይ ከተቀመጠው ሐረር ቢረ በነጥብ ዕኩል ሆኖ በጎል ብቻ ዘጠነኛ ላይ በ7 ነጥቦች የተቀመጠው ነቀምት ከተማ ክለቡን አሰልጣኙ እንዲያቆዩለት ወደ ቡድኑ መልሷቸዋል።

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ሌላኛው ላለመውረድ እየተጫወተ የሚገኘው ቦዲቲ ከተማ አሰልጣኝ አዲሱ ዶይሶን መሾሙ የሚታወስ ሲሆን ቤንች ማጂ ቡናም በአሰልጣኝ ሲሳይ አብረሀ ምትክ የቀድሞውን የባህርዳር ከተማ ረዳት አሰልጣኙ አብረሃም መላኩ መቅጠሩም ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...