መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ ሱለይማን ሀሚድ እና መቐለ 70 እንደርታ ይለያዩ ይሆን ?
መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሱለይማን ሀሚድ እና መቐለ 70 እንደርታ ይለያዩ ይሆን ?

አጋራ
አጋራ

ከሰሞኑ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ቅሬታ ውስጥ የገባው የመስመር ተከላካዩ ለክለቡ ደብዳቤ አስገብቷል።

ከሰሞኑ መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የመቐለ 70 እንደርታ እና የመስመር ተከላካዩ ሱለይማን ሀሚድ ጉዳይ በዋናነት ይነሳል። በፕሪምየር ሊጉ 22ኛ ሳምንት መቐለ 70 እንደርታ በድሬዳዋ ከተማ 2ለ1 በተሸነፈበት ጨዋታ በክረምቱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድኑን መቀላቀል የቻለው ሱለይማን ሀሚድ ተቀይሮ ገብቶ መጫወት የቻለ ሲሆን በገባባት ደቂቃ በእንቅስቃሴው ደስተኛ መሆን ያልቻሉት የመቐለ ደጋፊዎች ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የተጫዋቹን ስም እየጠሩ “የመጫወት ፍላጎት ከሌለህ ልቀቅልን ጉዳትም ካለብህ ክለቡ ውስጥ ህክምናህን መከታተል እንጂ ያለብህ ለምን ወደ ሀገርህ ትሄዳለህ” እያሉ ሌሎች ንግግሮችንም አካተው ሲቃወሙ በወቅቱ ሰምተናል።

ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር ያለ መግባባት ውስጥ ያሉት እና የቋሚ ተሰላፊነት ዕድልን እያገኘ ያለመሆኑ ቅሬታን የፈጠረበት የቀኝ መስመር ተከላካዩ ሱለይማን ሀሚድ ለክለቡ ይፋዊ ደብዳቤን አስገብቷል። “አሰልጣኙ እያሰለፈኝ አይደለም እኔ ደግሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ስለምፈልግ የመሰለፍ ዕድልን ማግኘት ካልቻልኩ ወደ ክለቡ መመለስ አልፈልግም መሰለፍ ስችል ብቻ ነው ወደ ክለቡ የምመለሰው” ሲል የገለፀ ሲሆን “በደጋፊውም እየተሰደብኩ በመሆኑ ከለላ የሚሆነኝን ማረጋገጫ እፈልጋለሁ ያ መሆን ካልቻለ በክለቡ መቀጠል አልችልም” ሲል አቤቱታውን አቅርቧል።

በውጤት መዳከር ውስጥ ሆኖ በደረጃ ሰንጠረዡ ወራጅ ቦታ ላይ ተቀምጦ የሚገኘው ተጫዋቹ ልክ ኪቲካ ጀማን እንደለቀቀው ሁሉ ከተከላካዩ ጋር ይለያያል ወይንስ ተስማምቶ ይቀጥላል የሚለው ጉዳይ በቀጣይ የሚጠበቅ ጉዳይ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...