አዳማ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ዋና አሰልጣኙን ከክለቡ አሰናብቷል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርከት ያሉ ዝውውሮችን ፈፅመው ወደ ውድድር ቢገቡም ከተጠበቀው በታች በፕሪምየር ሊጉ ላይ ውጤት ማምጣት የቻሉት አዳማ ከተማዎች በ33 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ካስቀመጡት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር ተለያይቷል።
የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ሰበታ ከተማ ፣ መቻል ፣ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ፣ በየመን ሊግ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጭምር በአሰልጣኝነት ያገለገሉት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከውጤት መጥፋት ባሻገር በቡድኑ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ተጫዋቾች በአሰልጣኙ ደስተኛ ያለ መሆናቸው ተደማምሮ በመጨረሻም የክለቡ ቦርድ ካደረገው ግምገማ በኋላ አሰልጣኙን አሰናብቷል።
በምትኩም ረዳቶቹ አሰልጣኝ ዳዊት ታደለ እና ዳዊት ሀብታሙ በቀጣዮቹ አራት ጨዋታዎች የሚያሳዩት ውጤት እየታየ ቡድኑን እንዲመሩ በቦታው ጊዜያዊ ሆነው በትግግዝ እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።
አስተያየት ይስጡ