መነሻ ገጽ ዜናዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግማሽ ደርዘን ግቦችን አስቆጥሮ ሲያሸንፍ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ጥሏል
ዜናዎችየሴቶች ፕሪምየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግማሽ ደርዘን ግቦችን አስቆጥሮ ሲያሸንፍ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ጥሏል

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን አጠናክሯል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታድየም ተደርገዋል።

በቀዳማዊ የዕለቱ ጨዋታ ልደታ ክፍለ ከተማን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ በስራ ይርዳው የ62ኛ ደቂቃ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል።

ከ07:00 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ለረጅም ሳምንታት ሊጉን ሲመራ ቆይቶ በ19ኛው ሳምንት መሪነቱን ያስረከበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሸገር ከተማ አቻ ተለያይቷል።

1 ለ 1 በተጠናቀቀው ጨዋታ ማርታ ወልዴ በ23ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ ሸገር ከተማን እስከ 89ኛው ደቂቃ መሪ አድርጎ ነበር።

ነገር ግን 90ኛው ደቂቃ ላይ ማህሌት ወርቁ በራሷ መረብ ላይ ባስቆጠረችው ግብ ጨዋታው 1 ለ 1 እንዲጠናቀቅ ሆኗል።

ከዚህ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ከአዳማ ከተማ የተጫወተው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 6 ለ 0 አሸንፏል።

ረድኤት አስረሳኸኝ 3 ግቦችን ስታስቆጥር ፤ መሳይ ተመስገን 2 እንዲሁም እሙሽ ዳንኤል ቀሪውን ግብ አስቆጥረዋል።

የዛሬ ውጤቶችን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ53 ነጥቦች የሊጉን መሪነት ይዞ ሲቀጥል ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ51 ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...