መነሻ ገጽ ዜናዎች የ24ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የ24ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ሲያም ሱልጣን (ድሬደዋ ከተማ): ቅዳሜ መጋቢት 5 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 82 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

2. ጌታነህ ታደሰ (ነገሌ አርሲ) /የቡድን መሪ/: ክለባቸው ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ከጨዋታ በኋላ የጠብ አጫሪነት ወይም የሃይለኝነት ድርጊት በመፈጸም በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ።
ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 13.3 ተ.ቁ 18 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 / አስር ሺህ / እንዲከፍሉ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

3. ዴሲሬ ፓስካል (ነገሌ አርሲ): ክለቡ ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 28 ኛ ደቂቃ ላይኳስ በእጅን በመጫወት የግብ የማግባት አድል በማበላሸት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ1 (ሀ) እና በተቁ 2 መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

4. ጄሮም ፍሊፕ (አርባምንጭ ከተማ): በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ።

  • ቅዱስ ጊዮርጊስ-አርባምንጭ ከተማ
  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-አርባምንጭ ከተማ
  • አርባምንጭ ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ
  • አርባምንጭ ከተማ-ኢትዮጵያ መድን

ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

5. አብዱል ጋንዩ (ኢትዮጵያ መድን ):  በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  • አዳማ ከተማ-ኢትዮጵያ መድን
  • ባህርዳር ከተማ-ኢትዮጵያ መድን
  • ኢትዮጵያ መድን -ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
  • አርባምንጭ ከተማ-ኢትዮጵያ መድን

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

6. አብዲ ዋበላ (መቐለ 70 እንደርታ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተ መልክቷል ።

  • መቐለ 70 እንደርታ-መቻል
  • መቐለ 70 እንደርታ-ፋሲል ከነማ
  • መቐለ 70 እንደርታ-ምድረ ገነት ሽረ
  • መቐለ 70 እንደርታ-ወላይታ ድቻ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

7. ተመስገን ተስፋዬ (መቐለ 70 እንደርታ): በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-መቐለ 70 እንደርታ
  • መቐለ 70 እንደርታ-ፋሲል ከነማ
  • ሃዋሳ ከተማ-መቐለ 70 እንደርታ
  • መቐለ 70 እንደርታ-ወላይታ ድቻ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

8. ፍፁም አለሙ (መቐለ 70 እንደርታ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  • መቐለ 70 እንደርታ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-መቐለ 70 እንደርታ
  • ኢትዮጵያ መድን -መቐለ 70 እንደርታ
  • ባህርዳር ከተማ-መቐለ 70 እንደርታ
  • መቐለ 70 እንደርታ-ወላይታ ድቻ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

9. ሙሉቀን አዲሱ (ወላይታ ድቻ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  •  ወላይታ ድቻ-መቐለ 70 እንደርታ
  • ወላይታ ድቻ-ሸገር ከተማ
  • ኢትዮ ኤሌትሪክ -ወላይታ ድቻ
  • ወላይታ ድቻ-ሲዳማ ቡና
  • መቐለ 70 እንደርታ-ወላይታ ድቻ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

10. ስምዖን ማሩ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።

  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-አዳማ ከተማ
  • ኢትዮጵያ መድን -ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
  • ሲዳማ ቡና-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ምድረ ገነት ሽረ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ድሬደዋ ከተማ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

11. ሙታክብዋ ጆኤል (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።

  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-መቐለ 70 እንደርታ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-አዳማ ከተማ
  • ሀዲያ ሆሳዕና-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ምድረ ገነት ሽረ
  • ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ድሬደዋ ከተማ

ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

12. ነገሌ አርሲ ክለቡ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ባደረገው የ24 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የነገሌ አርሲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት

  1. ዴሲሬ ፓስካል
  2. ዳግማዊ አርአያ
  3. ኢብሳ በፍቃዱ
  4. ዳዊት ተፈራ
  5.  ዘሩባቤል ፈለቀ

በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡

13. አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀዬ /ምድረ ገነት ሽረ (ዋና አሰልጣኝ ) /: ክለቡ ከከሲዳማ ቡና ጋር ጋር በነበረው የ24ኛ ሳምንት ግጥሚያ መጨረሻ ለአክሲዮን ማህበሩ ቀጥታ ስርጭት ቀረፃ አጋር ፈቃደኛ ሆነው መግለጫ ስላለመስጠታቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ።
ስለሆነም አሰልጣኙ በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር ደንብ ክፍል 3 ምዕራፍ 24 ተቁ 4 መሠረት ብር 10000 /አስር ሺህ / እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...