ከአሰልጣኙ ጋር የተለያየው ክለቡ በቀጣዩ ሳምንት አዲስ አሰልጣኝ ሊቀጥር ነው።
ከፋሲል ከነማ ጋር የተለያዩትን ዮሐንስ ሳህሌን በመተካት የክለቡ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ተደርገው የተሾሙት አሰልጣኝ አምሳሉ እስመለአለም ከፋሲል ከነማ ጋር በሁለተኛው ዙር በልምምድም ሆነ በጨዋታ ሜዳ ላይ አለመገኘታቸው አነጋጋሪ ነበር። ከተጫዋች ጋር ባለመግባባት በኋላም ከጥቅማ ጥቅም ጉዳይ ጋር በተያያዘ በክለቡ መቀጠል ያልፈለጉት አሰልጣኙ ክለቡን በይፋ መልቀቃቸው ታውቋል።
ከባህርዳር ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ስልጠናን ከጀመሩ በኋላ የባህዳር ተስፋ ቡድን አሰልጣኝ ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር የመቻል ረዳት ፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ የሳምሶን አየለ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን እንዲሁም የኢትዮጵያ ከሀያ አመት በታች ብሔራዊ ቡድንም ጭምር ረዳት ሆነው የሰሩት አምሳሉ እስመለአም ከአፄዎቹ ጋር ከተለያዩ በኋላ የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ረዳት ሆነው ዋልያዎቹን ለማገልገል በአሰልጣኙ ጥረት ቢደረግም ከሳምንት በፊት ካፍ ባወጣው የኤ ደረጃ ላይሰንስ ባለማሟላታቸው ብቻ ሳይካ ቀርቷል።
ፋሲል ከነማ በቀጣዩ ሳምንት አዲስ አሰልጣኝ እንደሚሾም ይጠበቃል።


