ለሹቲንግ ስታርስ እየተጫወተ የሚገኘው ተጫዋች አዞዎቹን ሊቀላቀል ነው።
ከሀገሩ ዲያፋ አካዳሚ በኋላ በ2013 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በከፍተኛ ሊጉ በሀምረሪቾ ዱራሜ በመጫወት ከሀገራችን እግር ኳስ ጋር የተዋወቀው የተከላካይ አማካዩ ቻርለስ ሪባኑ በመቀጠል በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ባህርዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ከተጫወተ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለአርባምንጭ ከተማ በመጫወት ቆይታን አድርጓል።
አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን ከቀጠረ በኋላ ከራበው ሦስት ነጥብ ጋር ሁለቴ የታረቀው እና ሁለት አቻ የወጣው ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት በሀገሩ ናይጄሪያ ለሹቲንግ ስታርስ በመጫወት ላይ የሚገኘውን እና ለክለቡ ከፈረመ ገና ስድስት ወራት ያልሞላውን አማካይ በድጋሚ ውሉን በማቋረጥ ወደ ክለቡ ሊያመጣው መቃረቡ ታውቋል።
አርባምንጭ ከተማዎች በተከታታይ ቀናት ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾችን እንደሚያካትቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።


