በሮዱዋ ደርቢ በበርካታ ደጋፊዎች የተደረገው የሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ሲዳማን ባለ ድል በማድረግ የደረጃ አናቱን በነጥብ ብልጫ መርቷል።
በሁለቱ ክለቦች ንግግር ከአዳማ ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾችን በሚይዘው የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ላይ በተደረገው የሊጉን መሪነዎች ያገናኘው ጨዋታ በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሔኖክ አበበ እየተመራ አስር ሰዓት ሲል ጀምሯል። እንደነበረው የደጋፊ ድባቡ በእንቅስቃሴ ብዙም ሳቢ ያልነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ በአንፃራዊነት ሲማ ቡናዎች ሻል ያለውን የማጥቃት አቅም ያሳዩበት ነበር ማለት ይቻላል።

ያሬድ ባዬ ከማዕዘን ተሻምታ የሀዋሳ ተከላካዮች በመዘናጋት ሆነው ያሬድ ባዬ ሞክሮ የግቡ የግራ ቋሚ ብረትን ገጭታ ከወጣችዋ ኳስ በኋላ 43ኛው ደቂቃ መሪ የሆኑበትን ጎል ወደ ካዝናቸው ከተዋል። ከግራ ተነስቶ በጥሩ የእግር ስር ወደ ሳጥን የላከለትን ኳሶ መስፍን ታፈሠ ብርሀኑ በቀለ የሀዋሳ ተከላካዮች ዝንጉነት ታክሎበት የግቡን አግዳሚ እና መረብ ኳሷ ነካክታ ግብ ሆናለች።
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው አጋማሽ በብዙ ተለውጠው የተመለሱት ሀዋሳ ከተማዎች በተለይ ሽመልስ በቀለ ወደ አማካይ ክፍሉ ከመጣ በኋላ ባደረገው እንቅስቃሴ 49ኛው ደቂቃ አንጋፋው አማካይ የሰጠውን ኳስ ተባረክ ሄፋሞ ጎል አድርጎት ጨዋታው ወደ 1ለ1 ቢለወጥም 55ኛው ደቂቃ ከእጅ ውርወራ የተገኘን ኳስ ደግፌ አለሙ ወደ ሳጥን ሲያሻማ የሀዋሳው ተከላካይ ሠለሞን ወዴሳ አቋቋምን የተመለከተው መስፍን ታፈሠ የልጅነት ክለቡ መረብ ላይ በግንባር አሳርፏል።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ ወደ መጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሀዋሳዎች በድግግሞሽ በተለይ ጌታነህ ከማዕዘን ሽመልስ አሻምቶ በግንባር ገጭቶ የግቡ ብረት ከመለሰበት አስቆጪ ሙከራ መልስ ለኋላ ክፍላቸው ጠንቃቆች የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች 2ለ1 በመርታት ሊጉ በሦስት ነጥብ ልዩነት መምራት ጀምረዋል።


