አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የዋሊያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

👉አሰልጣኝ ውበቱ 6 ድምጽ

👉አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ 1 ድምጽ

👉የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አንድ ቀን ዛሬ ሆኗል

 

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የዋሊያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሆኑ
ተረጋግጧል፡፡ ዛሬ ጠዋትም ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ተገኝቶ ውሉን መፈራረሙ ታውቋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው በምርጫው ሦስቱን አሰልጣኞች የገመገመ ሲሆን የሰበታ ከተማውን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በ6 ድምጽ ሲመርጥ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ 1 ድምጽ ብቻ አግኝቷል፡፡ አሰልጣኝ ውበቱ ከቀናት በፊት ለሀትሪክ መፅሄት በሰጠው ቃለምልልስ “የዋሊያዎቹ አለቃ የመሆን ዕድል ባገኝ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ከማርያኖ ባሬቶ ጊዜ ጀምሮ ስሜ እንደ ፔስ ሜከር ከአሰልጣኞቹ ጋር ሲጠራ ቆይቷል አንድ ቀን ግን ሃላፊነቱን እንደምይዝ ተስፋ አደርጋለሁ” ማለቱ ይታወቃል፡፡ የአሰልጣኝ ውበቱ “አንድ ቀን” ዛሬ ሆኖ ሃላፊነቱን ጀምሯል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport