አሰልጣኝ ውበቱ አባቱ ብሔራዊ ቡድኑን ለመረከብ ተቃርበዋል !

በፕርሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማን እያሰለጠኑ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ያሳለፉት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለመረከብ መቃረባቸው ተሰምቷል ፡፡ በዛሬው ዕለት በኮንትራት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረስ የሚችሉ ከሆነ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዋልያዎቹን እንደሚረከቡ ይጠበቃል ፡፡

 

ከአሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብርሀቱ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ያለ አሰልጣኝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታውን ለማድረግ የአርባ ስድስት ቀን እድሜ ብቻ ይቀረዋል ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor