የተጨዋቾች የደመወዝ ገደብ ከ2014 ጀምሮ እንዲነሳ ተወስኗል!

ሊግ ካምፓኒው
29 ሚሊየን ብር ገቢ እጠብቃለሁ አለ

* የተጨዋቾች የደመወዝ ገደብ
ከ2014 ጀምሮ እንዲነሳ ተወስኗል…


በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ስብሰባውን እያደረገ ያለው የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒ በ2013 ከሊጉ ስያሜ 8 ሚሊየን ብር እንደሚጠብቅ ገልጿል፡፡

ካምፓኒው ከክለቦች ክፍያ ከቲቪ መብትና ከሊጉ ስያሜ ጋር በአጠቃላይ 29 ሚሊየን ብር እንደሚጠብቅም አመራሮቹ ገልጸዋል፡፡ካምፓኒው ከዚህ በኋላም 5 ሰራተኛ እንደሚቀጥርና የራሱን ቢሮ እንደሚከራይ የተነገረ ሲሆን ሲያወዛግብ የነበረው የተጨዋቾች የ50 ሺ ብር የደመወዝ ገደብ በ2013 ባለበት እንዲቀጥል ከ2014 ጀምሮ ሁሉም እንደአቅሙ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስያሜያቸው ጥያቄ የተነሳባቸው ክለቦች በራሳቸው ፍቃድ ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ መወሰኑን በዝግ የተካሄደውን ስብሰባ ከፍተን ማረጋገጥ ችለናል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport