ቡናማዎቹ የተከላካያቸውን ውል አራዝመዋል !

 

የወጣት ተጫዋቾቻቸውን ውል ለበርካታ ዓመታት በማራዘም ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች አሁን ደግሞ የወሳኙን ተከላካያቸውን ወንድሜነህ ደረጄ ውል ለአራት ዓመታት ማራዘማቸውን የተጫዋቹ ወኪል ገልጿል ።

ባሳለፍነው ዓመት በኢትዮጵያ ቡና ምርጥ አቋም ካሳዩ ተጫዋቾች አንዱ ወንድሜነህ ደረጄ ሲሆን ክለቡም ይህን በማየት ከአቡበከር ነስሩ፣ አማኑኤል ዮሃንስ እና ሚኪያስ መኮንን ቀጥሎ በኢትዮጵያ ቡና ቤት ለረጅም ጊዜ የሚያቆየው ውል አቅርቦለታል ።

ከጣና ሞገዶቹ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው ወጣቱ ተከላካይ ወንድሜነህ ደረጄ እስከ 2017 የውድድር ዓመት በቡናማዎቹ ቤት የሚቆይ ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor