የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ መስከረም 11 ቀን 2013ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ባካሄዱት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል፡፡

1ኛ ካፍ በ Zone በሚያካሂዳቸው የማጣሪያ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች በሴካፋ ዞን በሚካሄዱት ውድድሮች በቀጣይ ሴካፋ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት እንዲሳተፉ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ CECAFA ውድድር በዚህ ዓመት እንዲሳተፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወስኗል፡፡

2ኛ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የ Club Licensing ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ የተወሰነ ሲሆን የሥራ አፈፃፀማቸው እየተገመገመ በየጊዜው ለስራ አስፈፃሚ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡
3ኛ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ ግብ ጠባቂ የነበረው ይልማ ከበደ (ጃሬ) በደረሰበት ህመም በአሁን ሰዓት ፓራላይዝድ ሆኖ ስለሚገኝ ለሕክምና እንዲረዳው የብር 50,000.00/ሀምሳ ሺህ ብር/ ድጋፍ እንዲደረግለት ተወስኗል፡፡

4ኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞችን በተመለከተ የቴክኒክ ኮሚቴው አሉኝ የሚላቸውን ምክረ-ሀሳቦችን በማዘጋጀት ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እንዲያቀርብ በመወሰን የዛሬው ስብሰባ ተጠናቋል።

via- EFF OFFICIAL

 

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor