አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ኤልመዲን መሃመድና ሃይሉ አድማሱ /ቻይና/ን ምክትሎቹ አድርጎ መረጠ፡፡

 

በዛሬው ዕለት አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናን ዋና አሰልጣኝ አድረገው መሾማቸው የተሰማው ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ምክትል አሰልጣኝ መሾማቸው ታውቋል ።

አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና የቀድሞ ተጫዋቾቹን  ኤልመዲን መሃመድ በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ሃይሉ አድማሱ/ቻይና/ በመብራት ሐይል እንዳሰለጠናቸው እሚታወቅ ሲሆን ዛሬ አሰልጣኙ በኤሌትሪክ ቤት መሾሙን ተክትሎ ምክትሎቹ አድርጎ መምረጡን ለማወቅ ተችሏል ።

ዋና አሰልጣኙ እና ምክትሎቻቸው በኢትዮ ኤሌክትሪክ ለሁለት ዓመታት እሚያቆያቸውን የፊርማ ስምምነት በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፈፅማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport