የኢትዮጵያ ቡና የስፖንሰር ሺፕ ሰምምነት !

የኢትዮጵያ ቡና የስፖንሰር ሺፕ ሰምምነት !

በአሁን ሰዓት በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ከሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር ጋር በመካሄድ ሲገኝ የተነሱት አንኳር ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው ።

 

ሀበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር ኢትዮጲያ ቡናን ለአንድ አመት በ28 ሚሊየን 250 ሺ ብር ስፖንሰር ያደርጋል ።

• የአንድ ዓመት የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ሲፈፀም ከ ሐምሌ 1 2012 እስከ ሰኔ 30 2013 ድረስ የ 18 ሚልዮን ስምምነት ተፈፅሟል ።

• ኢትዮጵያ ቡና በመጪው ዓመት በሚያዘጋጃቸው ዝግጅቶች ላይ የአራት ሚልዮን ብር ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል ።

• ኢትዮጵያ ቡና ለሚያዘጋጀም አመታዊ ሩጫ ሶስት ሚልዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተነግሯል ።

• ኢትዮጵያ ቡና በመጪው የውድድር አመት የሊጉ ሻምፒዮን የሚሆኑ ከሆኑ የ ሁለት ሚልዮን ሰባት መቶ ሺህ ብር እንዲሁም ሁለተኛ ሆኖ የሚያጠናቅቁ ከሆነ የዘጠኝ መቶ ሺህ ብር ጉርሻ እንደሚኖር ይፋ ሆኗል ።

• በእያንዳንዱ ጨዋታ የቡድኑ ውጤት በመመርኮዝ ከ ስድስት ሺህ እስከ ስምንት ሺህ ብር ጉርሻ እንደሚኖር ተገልጿል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor