ቢኒያም በላይ የሚገኝበት የሲውድኑ ክለብ 11 ተጨዋቾች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

 

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ቢኒያም በላይ የሚጫወትበት ኡሚ እግር ኳስ ክለብ 11 ተጨዋቾቹ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል። በዚህም ምክንያት ክለቡ የሚያደርገውን ጨዋታ እንዳራዘመ ለማወቅ ተችሏል።

ቢኒያም በላይ በቫይረሱ ከተያዙት ተጨዋቾች መካከል ይሁን አይሁን ይፋ የተደረገ ነገር የሌለ ሲሆን በቫያረሱ ከተያዙት ተጨዋቾች መካከል የአማካኝ ተጨዋቾች እንደሚገኙበት ታውቋል።

ቢኒያም በአሰልጣኝ ውበቱ አባት ከተመረጠው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ውጪ የተደረገ ሲሆን ምክንያቱን አጣርተን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።