መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ቀጣ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ቀጣ

አጋራ
አጋራ

👉“ቅጣቱ ከውላችን ውጪ በመሆኑ አልቀበለውም”
አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ

👉ዛሬ ምሽት ወደ አሜሪካ ይሄዳል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሀዋሳ የዘጠኝ ሳምንት ቆይታ በ16 ነጥብ 6ኛ ደረጃ የያዘው ኢትዮጵያ ቡና የስራ አመራር ቦርድ የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን የአምስት ቀን ደመወዝ ቀጣ።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ በአምስተኛው ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በወላይታ ድቻ 3ለ1 መሸነፉን ተከትሎ የክለቡ አመራር ለአሰልጣኝ ካሳዬ ውጤቱን እንዲያስተካክል የሚያሳስብ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቢያዘጋጅም አሰልጣኙ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ነገር ግን በተከታታይ የነበረውን የጅማ አባጅፋር፣ የመከላከያ፣ የድሬዳዋ ከተማና የወልቂጤ ከተማ ጨዋታዎችን ማሸነፉን ተከትሎ ጉዳዩ ሳይነሳ ቆይቷል። ነገር በ9ኛ ሳምንት በሀድያ ሆሳዕና መሸነፉን ተከትሎ “የተዘጋጀውን ደብዳቤ አለመቀበል የዲሲፕሊን ጥሰት ነው” በሚል ቦርዱ የአምስት ቀን ደመወዙን እንዲቀጣ ወስኖበታል። አሰልጣኝ ካሳዬ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤውን ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ትናንት ምሽት መቀበሉ ታውቋል።

አሰልጣኙ የሊጉን መቋረጥ ተከትሎ ዛሬ ምሽት ለዕረፍት ወደ አሜሪካ የሚጓዝ መሆኑ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...