መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | የሊጉ የሀዋሳ ቆይታ የመጨረሻ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል
ሀዋሳ ከተማአርባምንጭ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የሊጉ የሀዋሳ ቆይታ የመጨረሻ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

በዘጠነኛው ሳምንት እና በሊጉ የሀዋሳ ቆይታ የመጨረሻ የሆነው የሀዋሳ ከተማ እና የአርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ብሩክ በየነ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ ሀይቆቹ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል ።

ሀዋሳ ከተማ በስምንተኛው ሳምንት ከአዲስ አበባ ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ አንድ ቅያሪ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማዎች ከአዳማ ከተማ በተመሳሳይ አቻ ከተለያዩበት ጨዋታ ሁለት ቅያሪዎችን አድርገው ጨዋታውን ጀምረዋል ። ተጫዋቾቹም በሀዋሳ ከተማ በኩል ወንድማገኝ ማዕረግ በአርባምንጭ ከተማ በኩል ደግሞ ተካልኝ ደጀኔ እና አሸናፊ ፊዳ ናቸው ።

በጥሩ ፉክክር መንፈስ የተጀመረው ጨዋታ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በፈጣን እንቅስቃሴ የተካሄደ ነበር ። በሀዋሳ ከተማም ሆነ በአርባምንጭ ከተማ በኩል የነበረው ፈጣን እንቅስቃሴ ከመመስመሮች ተነስተው ወደ ግብ ክልል በሚደርሱ ኳሶች የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር በየበኩላቸው ጥረቶቸን ያደረጉበት ነበር ።

በመጀመሪያው አጋማሽ የተደረገው ቀዳሚው የግብ ሙከራ በ20ኛው ደቂቃ ላይ የተመዘገበ ነበር ። ሀቢብ ከማል ከሳጥኑ ቅርብ ርቀት የተገኘውን የቅጣት ምት ወደ ግብ ሞክሮት በግብ ጠባቂው መሀመድ ሙንታሪ ተይዟል ። ከውሀ እረፍት በኋላ ሀዋሳ ከተማዎች ወደ ግብ ክልል በመድረስ ረገድ ከተጋጣሚያቸው የተሻሉ ነበሩ ። ነገር ግን የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ አዳጋች ሆኖባቸው ነበር ። በ33ኛው ደቂቃ ላይ ኤፍሬም አሻሞ ከመስፍን ታፈሰ የደረሰውን ኳስ በሳጥኑ የቀኝ አቅጣጫ ሆኖ ወደ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወቷል ። የመጀመሪያው አጋማሸም ያለ ግብ ተጠናቀቀ ።

የሁለተኛው አጋማሽ የነበረው የጋለ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የቀጠለበት እና የግብ ሙከራዎችም የታጀበ ነበር ። በተለይም አርባምንጭ ከተማዎች በ49ኛው እና በ50ኛው ደቂቃ ላይ በተከታታይ ሶስት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለው ነበር ። በቅድሚያ ከግራ መስመር ወደ መለሕ የተሻገረውን ኳስ ፀጋዬ አበራ ወደ ግብ ሞክሮት በመሀመድ ሙንታሪ ተመልሷል በመቀጠልም በተመሳሳይ መስመር የተነሳውን ኳስ ሀቢብ ከማል ወደ ግብ የመታውን ኳስ እንዲሁም ፀጋዬ አበራ በድጋሚ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ መሀመድ ሙንታሪ በድንቅ ብቃት ግብ ከመሆን አድኗቸዋል ።

ሀዋሳ ከተማዎች በአመዛኙ በሚነጠቁ እና ከኋላ በሚነሱ ፈጣን ኳሶች የአርባምንጭ ተከላካዮችን መፈተን የቻሉ ሲሆን 67ኛው ደቂቂ ላይም በዚህ አጨዋወት ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። በወንድማገኝ ሀይሉ በመስፍን ታፈሰ እና በብሩክ በየነ ቅብብል እና በመጨረሻም በብሩክ ጨራሽነት ግቡ ተቆጥሯል ። ከግቡ አምስት ያህል ደቂቃዎች በፊትም ብሩክ በየነ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ያመከነው ኳስ ቀዳሚ ግብ መሆን የሚችል ነበር ።

ከግቡ በኋላ አዞዎቹ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ማድረግ ቢችሉም በሶስተኛው የማጥቃት ክፍል ሲደርሱ ኳሶቻቸው በሀዋሳ ከተማ ተከላካዮች ይመክኑባቸው ነበር ።
76ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር አቅጣጫ የተነሳው ኳስ በሀዋሳ ከተማ ተከላካዮች ሲመለስ ያገኘው በላይ ገዛኸኝ ወደ ግብ የሞከረውን ኳስ ተደጋጋሚ ኳሶችን ሲያድን የነበረው ሙንታሪ አድኖታል ። ቀጣዮቹ ደቂቃዎችም ሌላ ተጨማሪ ግብ ሳያስተናግዱ የዳኛው የጨዋታ ማጠናቀቂያ ፊሽካ ድምፅ ተሰምቷል ።

ውጤቱን ተከትሎም ሀዋሳ ከተማ ነጥቡን 14 በማድረስ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ሲል አርባምንጭ ከተማ በ11 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...