መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ደረጃውን ያሻሻለበትን ውጤት አስመዝግቧል
ባህርዳር ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ደረጃውን ያሻሻለበትን ውጤት አስመዝግቧል

አጋራ
አጋራ

በሊጉ የሀዋሳ ቆይታ የመጨረሻ ቀን ላይ በቅድሚያ አዳማ ከተማን ከባህርዳር ከተማ ያገናኘው ጨዋታ የቀድሞ ክለቡን በገጠመው ፋሲል ተካልኝ በሚመሩት አዳማ ከተማዎች የ1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

አዳማ ከተማ በስምንተኛው ሳመንት ከአርባምንጭ ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ከተጠቀሙት ቋሚ አስራአንድ አራት ቅያሪዎችን በማድረግ ዮናስ ገረመው ፤ ጀሚል ያዕቆብ ፤ አቡበከር ወንድሙን እና ዳዋ ሆቴሳን ጨዋታውን ሲያስጀምሩ በባህርዳር ከተማ በኩል ከፋሲል ከተሣ አቻ ከተለያየወሰ ቋሚ አሰላለፍ ሶስት ቅያሪዎችን ያደረጉ ሲሆን ተጫዋቾቹም መሳይ አገኘሁ ፤ ሳለአምላክ ተገኝ እና ፉአድ ፈረጃ ናቸው ።

በጨዋታው አዳማ ከተማዎች በተሻለ የተንቀሳቀሱበት ነበር ። በመጀመሪያው አጋማሽ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ በማጥቃቱ ረገድ አዳማ ከተማዎች ከተጋጣሚያቸው ባህርዳር ከተማ በልጠው በመገኝት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን አድርገዋል ። በባህርዳር ከተማ በኩል ቡድኑ በውድድር አመቱ ሲያሳይ ከነበረው አቋም አንፃር በዛሬው ጨዋታ የነበረው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ደከም ያለ ነበር ።

አዳማ ከተማዎች 4ኛው ደቂቃ ላይ ጥሩ ሊባል የሚችል የግብ ዕድልን መፍጠር ችለው ነበር ። አቡበከር ወንድሙ በቀኝ መስመር መናፍ አወልን አልፎ ለዳዋ ሆቴሳ ያደረሰውን ኳስ ዳዋ ወደ ግብ ለመምታት ሲሞክር ኳሱ በእግሮቹ መሀል አልፏል ።

ወደ ግብ ክልል ለመድረስ ቢጥሩም ሙከራዎችን ለማድረግ የተቸገሩት አዳማ ከተማዎች የመጀመሪያውን ኢላማውን የጠበሸ ሙከራ 25ኛ ደቂቃ ላይ አድርገዋል ። ከቀኝ መስመር በዮናስ ገረመው የተሻገረውን የቅጣት ምት ሚሊዮን ሰለሞን በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገውን ሙከራ ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤል ተቆጣጥሮታል ።

ከውሀ እረፋት በኋላ የጣና ሞገዶቹ የተሻለ መንቀሳቀስ ቢችሉም ወደ ማጥቃት ሲሸጋገሩ የነበረባቸው ክፍተት የግብ ሙከራዎች ማድረግ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል ። የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ በመልሶ ማጥቃት የሄደ ኳስ አሜ መሀመድ አግኝቶ ወደ ግብ ቢሞክረውም ኳሱ በሰለሞን ወዴሳ ተጨርፎ ለፋሲል በቀላሉ ደርሶታል ። የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል ።

በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ባህርዳር ከተማዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም ምንም መፍጠር ሳይችሉ በአዳማ ከተማዎች ብልጫ ተወስዶባቸዋል ። በዚህ አጋማሽም አዳማ ከተማዎች በተሻለ ወደ ፊት መሄድ ቢችሉም ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ለማደረግ እስከ 67ኛው ደቂቃ መጠበቅ የግድ ብሏቸው ነበር ።

ዳዋ ሆቴሳ ከቅጣት ምት ወደ ግብ የመታውን ኳስ ፋሲል ገብረሚካኤል ቢመልስበትም ኳሱ በአዳማ ከተማ ተጫዋቾች በድጋሚ ወደ ግብ መጥቶ ፋሲል መልሶ የተፋውን ኳስ ቢንያም አይተን በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር በሚሞክርበት ሰአት ተቀይሮ የገባው የባህርዳር ከተማው አጥቂ ተመስገን ደረሰ በአግሩ ጭንቅላቱን መቶታል በሚል የዕለቱ የመሀል ዳኛ ለአዳማ ከተማ የፍፁም ቅጣት ምት የሰጡ ሲሆን ዳዋ ሆቴሳም የተገኘውን ዕድል ወደ ግብ በመቀየር 71ኛ ደቂቃ ላይ አዳማ ከተማን መሪ አደረገ ።

መሪዎቹ አዳማ ከተማዎች ግቡንም ካስቆጠሩ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር የተንቀሳቀሱ ሲሆን በባህርዳር ከተማ በኩል ግን የጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች እስኪቃረቡ ያን ያህል የረባ እንቅስቃሴ ማድረግ ተስኗቸው ነበር ። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የተደረጉት ጥረቶች ፍሬ ቢስ ሆነው ጨዋታውን አዳማ ከተማዎች አሸንፈው ወተዋል ።

ይህም እስካሁን ከተደረጉ 7 የዘጠነኛው ሳምንት ጨዋታዎች በ1 ለ 0 ውጤት የተጠናቀቀ 5ኛ ጨዋታ ሆኗል ።

ውጤቱን ተከትሎም አዳማ ከተማ ነጥቡን 12 በማድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ ከነበረበት የወራጅ ቀጠና በመውጣት 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለ ሲሆን ባህርዳር ከተማ በበኩሉ በ14 ነጥብ በነበረበት 4ኛ ደረጃ ላይ የሚቆይ ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...