መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጲያ ቡና ካለበት የፋይናንስ ቀዉስ ለማዉጣት ከቡናዉ ሴክተር የሚገኘዉ ገንዘብ መጨመር አለበት ተባለ።

ኢትዮጲያ ቡና ስፖርት ክለብ ከረጅም አመታት ቆይታ በኋላ ዛሬ በቡና እና ሻይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስምንተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሂዷል። በጉባኤዉ በተለይም ክለቡ አሁን ካለበት ችግር በሚወጣበት እና በቀጣይ ስትራቴጂክ ዕቅድ ጉዳዮች ላይ ጉባኤተኛዉ ሰፊ ምክክር አካሂዷል።

በዋናነት አሁን ላይ ስፖርት ክለቡ የፋይናንስ ቀዉስ ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀዉስ በፍጥነት ለመዉጣት ደግሞ የቡናዉ ሴክተር ለክለቡ የሚደጉመዉ ገንዘብ በእጅጉ ማሻሻል እንዳለበት ጉባኤተኛዉ አንስቷል።

የቡናዉ ሴክተር ለክለቡ ከ14 አመት በፊት በ2004 በቶን ሰላሳ ብር ለክለቡ ገቢ ሲያደርግ ቢቆይም አሁን ላይ ካለዉ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ይህን ያክል አመት ሁሉ ለክለቡ የሚደጎመዉ ገንዘብ አለመጨመሩ ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነ ተነስቷል።

ከቡናዉ ሴክተር የሚገኘዉ ገንዘብ የሚጨምር ከሆነ ኢትዮጲያ ቡና በቀጣይ የፋይናንስ ጥያቄ የማይነሳበት ክለብ ማድረግ ይቻላልም ተብሏል።

ጭማሬዉ እስካሁን ሳይደረግ መቆየቱ ልክ እንዳልሆነ የተረዳዉ የቡና እና ሻይ ተወካይ ችግሩን በመረዳት ከቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በመነጋገር በአፋጣኝ ጭማሪ እንደሚደረግ ያላቸዉን እምነት ገልፀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...