መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና “ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

አጋራ
አጋራ

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ቡናን ከምስረታው አንስቶ በተለያዩ ሀላፊነት ከአርባ አመት በላይ መርተው ከፕሬዝዳንትነት የለቀቁት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ምን አሉ ?

“ኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ክለብ ነው። ለዚህ ክለብ ብዙ ነገር ሆነው ያለፉ ብዙ ሰዎች አሉ ፤ እነሱን እያሰብኩ ስፅፍ ፣ ሳወጣና ሳወርድ ነበር። ዛሬ ቦታዬን የምለቀው ደስተኛ ሆኜ ነው። ምክንያቱም ክለቡ ወደ አስተማማኝ እጅ ነው የተሸጋገረው። አሁን ትልቁ ነገር ክለቡ መልካም ሰዎች እጅ መውደቁና ቀጣይነቱ መረጋገጡ ነው። ኢትዮጵያ ቡና አይፈርስም።

“ሌላው ነገር ብዙ ያስቀየምኳቸው ሰዎች አሉ ፤ እነሱን ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ። ስናገር ፣ አንዳንድ ውሳኔዎችን ስወስን ፣ ሀሳብ ይዘው የሚመጡ ሰዎችን ያለመስማት ፣ ያለማባበልና ቁጭ አድርጎ ያለማወያየት ችግር ነበረብኝ። ዕድሉን አልሰጣቸውም ነበር። ለዚህ ከልቤ ይቅርታ እጠይቃችኋለሁ። ደጋፊዎቻችንንም ይቅርታ እጠይቃለሁ።

የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ሁልጊዜም ውጤትን ይፈልጋሉ። አንዳንድ ጊዜ የሚፅፉትና የሚናገሩት ከውጤት ማጣት የተነሳ እንደሆነ ይገባኛል። ነገር ግን ሁሉም ሰው ይሄንን ይሸከማል ማለት አይቻልም። አንዳንድ ሰው ቆዳው ስስ ነው ፤ ቶሎ ሊከፋ ይችላል። ስለዚህ ከመፃፍና ከመናገር በፊት ትንሽ ማስተዋል ቢኖር መልካም ነው እላለሁ። ይህ ትልቅ ክለብ ነው ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...