ኢትዮጵያ ቡናን በርከት ላሉ ዓመታት በስራ አስኪያጅነት መምራት የቻሉት አቶ ገዛሀኝ ወልዴ ለኢትዮጵያ ቡና ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ተቀባይነት ማግኘት ችሏል ።
አቶ ገዛኸኝ እና ቦርዱ በጋራ ስምምነት መለያየታቸው የተገለፀ ሲሆን አቶ ገዛኸኝ በአሁኑ ሰዓት በሀገር ወጪ የሚገኙ ሲሆን ወደ ሀገር ሲመለሱ የመልቀቂያ ደብዳቤውን የሚቀበሉ ይሆናል ።
አቶ ገዛኸኝ ኢትዮጵያ ቡናን ለ በርካታ ዓመታት መምረራት የቻሉ ሲሆን በተደጋጋሚ በቅርቡ ከደጋፊዎች ተቃውሞ ሲቀርብባቸው ተስተውሏል ።
የኢትዮጵያ ቡና ቦርድ የፊታችን ሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን አዲስ ስራአስኪያጅ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል ።
- ማሰታውቂያ -



