አሰልጣኝ ዓብይ ካሳሁንን ያሰናበተው ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከጫፍ መድረሱ እየተነገረ ነው።
ከታማኝ ምኝጭ በተገኘ መረጃ የበርካታ አሰልጣኞች ሰም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እየተያያዘ ሲሆን ከካምፓላ ሲቲ ጋር የተለያየው አሰሕጤኝ ፍሬው ሃ/ገብርኤል የቡናማዎቹ ቀጣይ አሰልጣኝ ሊሆን መሆኑ እየተነገረ ነው።
ከደደቢት ከኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም ካምፓላ ሲቲ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው አሰልጣኝ ፍሬው ስምም በስፋት እየተነሳ መሆኑ ተሰምቷል።
አሰልጣኝ ፍሬው ሃላፊነቱን ከያዘ ከአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው
/ማንጎ/ እና ከአሰልጣኝ መሰረት ማኔ በመቀጠል ከሴት ቡድን አሰልጣኝነት ወደ ወንዶች ቡድን ሃላፊነት የሚይዝ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ቡና ቦርድ ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ የሚመረጠውን አሰልጣኝ የሚያሳውቅ ሲሆን ተመራጩ አሰልጣኝ የፊታችን ረቡዕ ከመቻል ጋር በሚኖር ጨዋታ ቡድኑን መምራት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
አሰልጣኝ ፍሬው የኤ ላይሰንስ ካላቸው አሰልጣኞች መሃል አንዱ መሆኑም ይታወቃል


