የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ቢንያም ፍቅሩ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) : ሐሙስ ታህሳስ 16 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+3 ኛ ደቂቃ ላይየተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ሐብታሙ ታደሰ (ሲዳማ ቡና) : አርብ ታህሳስ 17 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+1 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ፡
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ራምኬል ጀምስ (ኢትዮጵያ ቡና) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ማሰታውቂያ -
- ኢትዮጵያ ቡና-ቅዱስ ጊዮርጊስ
- አዳማ ከተማ-ኢትዮጵያ ቡና
- ኢትዮጵያ ቡና ሀዲያ ሆሳዕና
- ኢትዮጵያ ቡና-ድሬደዋ ከተማ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል
4. ጊት ጋትኩት (መቐለ 70 እንደርታ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል።
- ምድረ ገነት ሽረ -መቐለ 70 እንደርታ
- መቐለ 70 እንደርታ -መቻል
- መቐለ 70 እንደርታ-ሃዋሳ ከተማ
- ወላይታ ድቻ- መቐለ 70 እንደርታ
- አርባምንጭ ከተማ-መቐለ 70 እንደርታ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5. ናትናኤል ዘለቀ (ሸገር ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
- ሸገር ከተማ-አዳማ ከተማ
- ሸገር ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና
- አርባምንጭ ከተማ-ሸገር ከተማ
- ነገሌ አርሲ-ሸገር ከተማ
- ሸገር ከተማ-ሃዋሳ ከተማ
ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
6. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ11 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 አቡበከር አዳሙ
2 ኤርሚያስ ሹምበዛ
3 ራምኬል ጀምስ
4 ይታገሱ ታሪኩ
5 እንዳሻው እሸቴ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7. ሸገር ከተማ ክለቡ ከሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ11 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሸገር ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ቡልቻ ሹራ
2 ዘነበ ከድር
3 ናትናኤል ዘለቀ
4አድናን ረሻድ
5 ምስጋና ሚልኪያስ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
8. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ11 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ያሬድ ከበደ
2 ፍቃዱ መኮንን
3ብሩክ እንዳለ
4 ሙሉአለም መስፍን
5 ፍሬው ሰለሞን
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡


