መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሊግ ካምፓኒ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞን በድጋሚ የማህበሩ ሰብሳቢ አድርጎ መረጠ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሊግ ካምፓኒ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞን በድጋሚ የማህበሩ ሰብሳቢ አድርጎ መረጠ

አጋራ
አጋራ

👉”ክለቦች የነቀዙ ተጨዋቾችን እያፈራን መሆኑን እንወቅ በትናንቱ ጨዋታ 8 ሚሊዮን ብር ያወጣ ተጨዋች ነበረን…?” መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ
/የአክሲዮን ማህበሩ ሰብሳቢ/

👉”ለክለቦች የምለው ስታዲየም አትገንቡ ባስገባችሁት ገንዘብ ግን እስቲ ሌላው ቢቀር ሜዳውን ስሩ “”
አቶ ኢሳያስ ጅራ
/ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት/

*…..”ቤትኪንግ” ከስሬያለሁ ብሎ አዲስ አበባን
መልቀቁ ተነገረ….

የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞን በድጋሚ አክሲዮን ማህበሩን በቦርድ ሰብሳቢነት እንዲመሩ መረጠ።

ዛሬ በካፒታል ሆቴል በተካሄደው አራተኛው መደበኛና ሁለተኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 16ቱ የሊግ ኩባንያ ተወካዮች በተገኙበት በተካሄደው ምርጫ ምርጫ መሰረት የኢትዮጵያ መድኑ መንግስቱ መሃሩ፣ የፋሲል ከነማው አቢዮት ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ቡናው መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣ የወልቂጤ ከተማው ጌቱ ደጉ፣ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ንዋይ በየነ፣ የባህርዳር ከተማው ልዑል ፍቃዱና የወላይታ ድቻው አሰፋ ሆሲሶን የቦርድ አመራር አደርጎ መርጧል። እነኚሁ ተመራጮች በግላቸው ባደረጉት አጠር ያለ ውይይት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞን /ኢት.ቡና/ ረዳት ፕሮፌሰር ጌቱ ደጉ / ከወልቂጤ/ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።
በጉባኤው ውሳኔ መሰረት የድሬዳዋ ከተማው አቶ ሱልጣን አሊዬ፣ የሀዋሳ ከተማዋ ደጊቱ ጫሌና የአርባምንጭ ከተማው ደምሴ አድማሱ ባመጡት ድምጽ መሠረት ተጠባባቂ ሆነው ተመርጠዋል።

መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ከምርጫው በኋላ ባደረጉት ንግግር “ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ከስሬያለሁ ብሎ ሀገር ለቆ ወጥቷል በአዲስ አበባ እየተጫወትን አይደለም ሜዳ የለም በአዲስ አበባ ኳስ እንዲኖር አይፈቀድም እንዴ ..?
የአዲስ አበባ ስታዲየም እየተሰራ ነው እያሉን 2 አመት ሞላው 3ኛ አመት እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ ሜዳ ሳይኖር እግርኳስ የለም እንደውም ሳንሰራ እንደምንበላ ሁሉ ይቆጠር ያለ ሜዳ ኳስ አይሆንም ትላንት ምሽት ብሄራዊ ቡድናችን በመሸነፉ ቅር ብሎኛል ብሄራዊ ቡድኑ ማላዊ ላይ ግብጽን 2 ለ0 ሲረታ ተስፋ አድርገን ነበር አሰልጣኞቹ 4 ወይም 6 ነጥብ እናገኛለን ቢሉንም አልተሳካም ውጤቴ ሲጠፋ አሰልጣኙን መተቸት እንተውና መጀመሪያ እኛ ክለቦች ከዚያ ተጨዋች ከዚያ አሰልጣኝ እያልን መጠየቅ ይሻላል ክለቦች የነቀዙ ተጨዋቾችን እያፈራን መሆኑን እንወቅ በትናንቱ ጨዋታ 8 ሚሊዮን ብር ያወጣ ተጨዋች ነበረን…? እናም በሚቀጥሉት 3 አመታት ራሳችንን ከማጠናከር ውጪ ለብሄራዊ ቡድን ማሰብ አለብን አሁንም ለሰኞ ጨዋታ መልካም ውጤት እመኛለሁ” በማለት ተናግረዋል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ በመዝጊያ ንግግራቸው “ትልልቅ አመራር እንዳላችሁ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ተቋም መሆናችሁንም ጭምር አሳይታችኋል ሊጉ ሲሰራ የፌዴሬሽኑን፣ የካፍና የፊፋን ህግ አክብሩ የእናንተን ማንዴት ያልሆነ ስትነኩ ሌላ ጫጫታ እንዳይፈጥር ማሰብ አለባችሁ በኛ በኩል ያለውን የህግ ክፍተት አንስተን መርምረን እናስተካክላለን ውድድር ስትመሩ ጥንቃቄ ይዛችሁ ምሩ ይህን አስተካክሉ በስልጣን ሂደታችሁ ተስማምታችሁ መስረታችሁ ዕድገታችሁን ያሳያል በቀጣይ የምርጫ ሂደት ሰነድ ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት የመተዳደሪያ ደንብ ጉዳይም እኛ በትኩረት የምናየው ጉዳይ ነው። ስለ ሀገሪቱ ስታዲየሞች ጉዳይ ያለው ጥያቄ በእኔ ስር አይወሰንም ስለ ቡድናችን ስናነሳ ወደቤቱ ይመለስ እሱን አግዙን ያ ሊያሳስበን ይገባል ፌዴሬሽኑ ከሊጉ ጋር እጅና ጓንት ሆነን መጓዝ ግዴታው ነው ተመራጮቹ ስልጣን ሳይሆን ሃላፊነት ነው የተቀበላችሁት በፋይናንስና በክለብ ላይሰንሲንግ ጉዳይ የሚጠበቅባችሁን ማሟላት ያስፈልጋል በአዲሱ አመራር ሊጉ ከተቀበላችሁበት ዝቅ ብሎ ወረዶ ከተገኘ እንወቅሳለን ካለበት ከፍ ካደረጋችሁት እናመሰግናለን ለክለቦች የምለው ስታዲየም አትገንቡ ባስገባችሁት ገንዘብ ግን እስቲ ሌላው ቢቀር ሜዳውን ስሩ “” በማለት ጠንካራ ንግግር አድርገዋል።በዚሁ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የአክሲዮን ማህበሩ የፋዬናንስ ሂሳብ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በ2013 እና 2014 ከታክስ በፊት 24 ሚሊዮን 429,572 ብር ማትረፉ ተገልጿል። በዚህም ሪፖርት በ2013 120 ሚሊዮን በ2014 149 ሚሊዮን ብር ለክለቦቹ መከፋፈሉም ይፋ ተደርጓል። በ2013 5 ሚሊዮን ብር በ2014 ደግሞ 6 ሚሊዮን ብር በታክስ መልክ ለመንግስት መከፈሉም ተገልጿል።

በጉባኤው ላይ ከፍተኛ ክርክር ያስነሳው የአክሲዮን ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ በዚህ ጉባኤ ላይ ቀርቦ ይጽደቅ ወይስ ወደ ሰኔ ወር ይዛወር በሚል የቀረበው አጀንዳ ሲሆን ከከፍተኛ ክርክር በኋላ በመጪው ሰኔ ቀርቦ እንዲጸድቅ ውሳኔ አግኝቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...