የባህርዳር ስታዲየም ከ22ኛ ሳምንት ጀምሮ ያሉትን ጨዌታዎች እንዲያስተናግድ ሊግ ካምፓኒው ወሰነ ።
የሊግ ካምፓኒው አመራሮችና ባለሙያዎች የባህርዳር ስታዲየም በተያዘለት ቀጠሮ መሠረት ጨዋታውን እንዲያስተናግድ መምረጣቸው ታውቋል። በአዳማ እየተካሄደ ያለው ውድድር 21ኛው ሳምንት ድረስ ከተካሄደ በኋላ ከአምስት ቀን ዕረፍት በኋላ ከ22ኛው ሳምንት ጀምሮ በባህርዳር እንደሚያካሂድ ታውቋል።
አወዳዳሪው አካሉ ፓውዛ በሌለው የባህርዳር ስታዲየም ጨዋታው እንዲካሄድ በመፍቀዱ ውድድሩ ጠዋት 4 ሰአትና ቀን 9 ሰአት የመካሄዱ ዕድሉ ሰፍቷል ተብሏል።
ሊግ ካምፓኒው በቀጣይ የሰአቶቹን አማራጩን ካየ በኋላ ሰአቱን በይፋ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ