በ2023 በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር በኮትዲቯር አዘጋጅኘት ለሚደረገው በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ 24 ሀገራትን የሚለየው ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ ምሽት ከ2:30 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ይደረጋል ።
በማጣሪያው ላይ 48 ሀገራት በ12 ምድብ ተከፍለው የሚወዳደሩ ሲሆን ከየምድቡ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ ሀገራት የአቢጃን ትኬታቸውን ይቆርጣሉ ።
አርባ ስምንቱ ሀገራት ባለፈው ወር የፊፋ የሀገራት ደረጃን መሰረት ባደረገ መልኩ በ4 ቋት የተከፋፈሉ ሲሆን ዋልያዎቹ በቋት አራት ላይ ተመድበዋል ።
ቋት 4
ታንዛንያ
መካከለኛው አፍሪካ
ሱዳን
ሩዋንዳ
ብሩንዲ
ኢትዮጵያ
እስዋቲኒ
ሌሶቶ
ቦትስዋና
ላይቤሪያ
ደቡብ ሱዳን
ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
- ማሰታውቂያ -
በማጣሪያው ላይ አዘጋጇ ሀገርም የምትሳተፍ ሲሆን በምድቡ አንድኛ ወይም ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቅ ካልቻለች ከሌሎቹ 11 ምደቦች በሁለተኛ ደረጃ ካጠናቀቁ ሀገራት ዝቅተኛ ውጤት ያለው ብሄራዊ ቡድን ከማጣሪናው የሚወድቅ ይሆናል ።