መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | ቡናማዎቹ የጦና ንቦቹን ረተዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ቡናማዎቹ የጦና ንቦቹን ረተዋል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን አድርገው በሮቤል ተክለሚካኤል ብቸኛ ግብ ቡናማዎቹ ሶስት ነጥብ ይዘው ወተዋል ።

ኢትዮጵያ ቡናዎች በ18ኛው ሳምንት ሰበታ ከነማን ሲረቱ ከነበረዉ ምርጥ 11 ሁለት ለውጦችን በማድረግ በገዛኸኝ ደሳለኝ እና አቡበከር ናስር ምትክ ቴዎድሮስ በቀለን እና እንዳለ ደባልቄን ያሰለፉ ሲሆን ወላይታ ድቻዎች በሳምንቱ ከአዳማ ከነማ ጋር ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ላይ በተጠቀሙት የመጀመሪያ አሰላለፍ ላይ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ጨዋታውን ጀምረዋል ።በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡናዎች ከፍተኛ የኳስ ቁጥጥር ወስደው የተጫወቱ ሲሆን ወላይታ ድቻዎች የቡናማዎቹን የኳስ ምስረታ በማቋረጥ አልፎ አልፎ ጥቃቶችን ለመሰንዘር ሞክረዋል ። በተጨማሪም የኋላ ክፍላቸው ጥንካሬ የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች በቀላሉ የግብ ሙከራዎችን እንዳያደርጉ አድርጓቸው ቆይቷል ።

በ16ኛው ደቂቃ ላይ አበባየሁ አጪሶ የኢትዮጵያ ቡናውን ተከላካይ ቴዎድሮስ በቀለን ቀምቶ ወደ ሳጥን ይዞ የገባውን ኳስ መሞከር ቢችልም ኳሱ ኢላማውን የጠበቀ አልነበረም ። በ24ኛው ደቂቃ ላይ ወላይታ ድቻዎች በመስመር በኩል የፈጠሩትን የግብ አጋጣሚም ለመጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል ።

የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ የተቸገሩት ቡናማዎቹ በ40ኛው ደቂቃ ላይ አስራት ቱንጆ በራሱ ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘውን የቅጣት ምት ወደ ግብ በቀጥታ ልኮት በፅዮን መርዕድ በተመለሰበት ኳስ የአጋማሹ ብቸኛ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ችለዋል ።በሁለተኛው አጋማሽ ቡናማዎቹ ጫና ማሳደራቸውን በመቀጠል ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ ወደ ወላይታ ድቻ የግብ ክልል መቅረብ ችለው ነበር ። በተለይም በግራ መስመር ላይ በዊልያም ሰለሞን አማካኝነት በተደጋጋሚ የጦና ንቦቹን የተከላካይ መስመር መፈተን ችለዋል ። በ53ኛው ደቂቃ ላይ ዊልያም ሰለሞን ሶስት የወላይታ ድቻ ተከላካዮችን በማለፍ ወደ ሳጥን ይዞ የገባውን ኳስ በአንተነህ ጉግሳ ሲመለስበት በቅርብ የነበረው እንዳለ ደባልቄ ወደ ግብ መሞከር ቢችልም ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድ መልሶበታል ።

በ61ኛው ደቂቃ ላይ አቡበከር ናስርን በእንዳለ ደባልቄ ተክተው ያስገቡት ቡናማዎቹ የበለጠ ጫና መፍጠር የቻሉባቸውን አጋጣሚዎች መፍጠር ችለዋል ።በወላይታ ድቻ በኩል በመከላከል ላይ ጠንከር ብለው የተጋጣሚያቸውን የማጥቃት ሂደት ለማቋረጥ ጥረቶችን በማድረግ አልፍ አልፎ ረጃጅም ኳሶችን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ቡና የግብ ክልል ለመድረስ ሞክረዋል ። በ74ኛው ደቂቃ ላይም በፈጣን መልሶ ማጥቃት ወደ ኢትዮጵያ ቡና ሳጥን በመግባት በያሬድ ዳዊት ያደረጉት ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ በበረከት አማረ ተመልሷል ።

በ78ኛው ደቂቃ ላይ የወላይታ ድቻው ተከላካይ አንተነህ ጉግሳ ኳሱን ለማራቅ ሲሞክር ዊልያም ሰለሞን አግኝቶ ለአቡበከር ናስር ያቀበለውን ኳስ ባሳለፍነው ጨዋታ ከረጅም ርቀት ላይ ድንቅ ግብ ያስቆጠረው ኤርትራዊው ሮቤል ተክለሚካኤል ተቀብሎ ኳስ እና መረብን አገናኝቷል ።

በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ የጦና ንቦቹ ግብ ለማግኘት ቀደም ብሎ ከነበራቸው እንቅስቃሴ በተሻለ ወደ ፊት በመንቀሳቀስ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ቢጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል ።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 27 በማድረስ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ በበኩሉ በ32 ነጥብ በ3ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።በ20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ቅዳሜ ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ጅማ ከአባጅፋር ሲጫወት በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ሰበታ ከተማን ይገጥማል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...