ሶስቱ የትግራይ ክለቦች መቅረታቸው ተረጋገጠ

*.. አዳማ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማና ጅማ አባጅፋር በሊጉ የመቆየት እድል አገኙ

ከሃምሌ 1-15/2013 ድረስ ለ2014 የውድድር አመት የመመዝገብ እድል የነበራቸው መቀለ 70 እንደርታ፣ ስሁል ሽረና ወልዋሎ አዲግራት የመጨረሻ ቀነገደቡ በሆነው በዛሬው ዕለት አለመመዝገባቸው ታውቋል።

ይህን ተከትሎ በሀዋሳ ለተማ በተደረገው የማጣሪያ ውድድር ከ1-3 የወጡት አዳማ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማና ጅማ አባጅፋር ያገኙትን ወርቃማ እድል ተጠቅመዋል። የፕሪሚየር ሊግ ኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰይፈ ክፍሌ እንደተናገሩት” ለሶስቱ የትግራይ ክለቦች የሰጠነው የመመዝገቢያ ቀነገደብ ተጠናቋል።

በዚህ መሰረት ፌዴሬሽኑ 3ቱ የሚተኩትን ክለቦች ዝርዝር እንዲሰጠን ጠይቀን ዛሬ ደርሶናል ስለዚህ አዳማ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማና ጅማ አባጅፋር የመመዝገቢያ 200ሺህ ብር እየከፈሉ እንዲመዘገቡ ነገ ደብዳቤ ይጻፍላቸዋል” ሲሉ አስረድተዋል። አቶ ክፍሌ አክለውም” በቀጣዩ አመት 16 ክለቦች የሚወዳደሩ ይሆናል 13ቱ ክለቦች ከፍለው ተመዝግበዋል ሶስቱም በቀጣይ ሳምንት ይመዘገባሉ ብለን እናምናለን የነርሱ ምዝገባ እንደተጠናቀቀ አጠር ባለ ፕሮግራም የእጣ ማውጣት ስነስርአት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *