ኢትዮጵያ ቡና የነባር ተጫዋቹን ዉል አድሷል !!

ኢትዮጵያ ቡናዎች በቀጣዩ አመት ለሚጠብቃቸው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታወች ይረዳቸዉ ዘንድ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸዉ ከመቀላቀል ባሻገር የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

በዛሬዉ ዕለት ደግሞ በ2012 የዉድድር አመት ቡድኑን የተቀላቀለዉ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ እንዳለ ደባልቄ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሶስት ተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን የኮንትራት ዉል ተፈራርሟል።

ያለፉትን ሁለት የዉድድር ዘመናት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቆይታ የነበረዉ አጥቂዉ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለመቆየት ዉሉን ማደሱን ክለቡ ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *