ፈረሰኞች አዲስ አሰልጣኝ ሾመዋል !

ለወራት ያክል ያለ ዋና አሰልጣኝ የቆዩት ፈረሰኞቹ በመጨረሻም የ64ዓመቱን ስርቢያዊ ዝላትኮ ክራምፖቲች መሾማቸው ታዉቋል።

አስልጣኙ የስርቢያን ከ17 ዓመት በታች እና ከ19 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በአፍሪካ የተለያዩ ቡድኖችን በማስልጠን የካበተ ልምድ ያላቸው ናቸው ካስለጠኑባቸው ክለባች መካከልም የሯንዳው ዜስኮ ዩናይትድ ፣ዲሞክራቲክ ኮንጎ ቲፒ ማዜንቤ ፣የደቡብ አፍሪካው ፖሎ ኪዊን ሲቲ እና የታንዛኒያው ያንጋ አፍሪካ ይገኙባችዋል ።

በዘንድሮው የዉድድር አመት በሊጉ ወጣ ገባ አቋምን በማሳነየት አመቱን ያጠናቀቁት ፈረሰኞቹ ለቀጣዩ የዉድድር አመት ተሻሽለዉ ለመቅረብ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ መሆናቸው ይታወቃል። በቅርቡም አሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ይጠበቃል ።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *