የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደብዳቤ ቁጥር 2/ኢ.እ.ፌዴ.6/2441 በቀን 09/10/2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የውድድርና ስነ-ስርዓት ኮሜቴ በ16/09/2014 ዓ.ም የወሰነውን ውሳኔ የሚሽር ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር መላኩ ይታወቃል።
በዛሬው እለት የአክስዮን ማህበሩ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ለክለቡ እና ለተጫዋቹ ባሳወቀው መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ በተጫዋች ጌታነህ ከበደ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ የሻረበት መንገድ የህግ ክፍተትና የአካሄድ ችግር ያለበት መሆኑን በመግለፅ የውድድርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ከዚህ በፊት በተጫዋቹ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ(የሶስት ጨዋታ እና የገንዘብ ቅጣት) የፀና መሆኑን አሳውቋል።
አስተያየት ይስጡ