የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት እና የማጠቃለያ መርሃ ግብር የፊታችን ሀሙስ በድሬዳዋ ከተማ ይካሄዳል።
መስከረም 9/2017 ዓ.ም በድሬደዋ ከተማ በሚደረገው የሽልማት ስነስርዓት በ7 ዘርፍ የአመቱ ኮከቦች ይሸለማሉ ፤ ለተሳታፊ ክለቦች እና ባለሜዳዎችም የገንዘብ ክፍፍል ይደረጋል ሲል ፕሪሚየር ሊጉ አሳውቋል።
የሽልማት ስነስርዓቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ የ2017 ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሚጀመርባት ድሬደዋ ከተማ የሚደረግ ይሆናል።
ከ7ቱ የሽልማት ዘርፎች የአመቱ ኮከብ የመሃልና ረዳት ዳኞች ምርጫ አነጋጋሪ ሲሆን ረጅሙን የውድድር አመት የመራው የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ በነበረው በኮሚሽነር ሸረፋ ደሌቾ የሚመራው ኮሚቴ ወይስ አጠር ላለ ጊዜ ኮሚቴውን የመራው የኢንተርናሽናል ረዳት አርቢትር ሸዋንግዛው ተባባል የሚመራው ኮሚቴ ምርጫውን ያካሂዳል የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል።
- ማሰታውቂያ -
የምርጫ ሂደቱ በነጻና ግልጽ በሆነ የምርጫ መስፈርት የሚካሄድ እንዲሆን የስፖርት ቤተሰቡ ጥያቄ ሆኗል።