የ2024 ዳይመንድ ሊግ የመጨረሻ ውድድሮች በቤልጅየም ብራስልስ ከተማ በመደረግ ላይ ናቸው።
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተጠባቂ በነበሩበት የወንዶች 5 ሺህ ሜትር አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ12:43.66 በቀዳሚነት አጠናቋል።
የዳይመንድ ሊግ 18ኛው ኢትዮጵያዊ አሸናፊ የሆነው በሪሁ አረጋዊ የአልማዝ ዋንጫ እና የ30 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል።
በተጨማሪም ሀጎስ ገብረሕይወት በ12:44.25 እንዲሁም ጥላሁም ሐይሌ በ12:45.63 የሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ወድድሩን አጠናቀዋል።
- ማሰታውቂያ -
ውጤታቸውን ተከትሎም ሀጎስ ገብረሕይወት የ12 ሺህ ዶላር እንዲሁም ጥላሁን ሐይሌ የ7 ሺህ ዶላስ ተሸላሚ ሲሆኑ የአምስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ዮሚፍ ቀጄልቻ የ2,500 ዶላር አሸናፊ ሆኗል።
በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ጌትነት ዋለ እና ሳሙኤል ፍሬው የ7ኛ እና 8ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ የ1,500 እና 1,000 ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል።
በሴቶች 800 ሜትር ደግሞ ሀብታም አለሙ በ1:59.81 የ6ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ የ2 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆናለች።