*…..የ8 አመት የስትራቴጂክ ዕቅድ መዘጋጀቱ ይፋ
አድርጓል…
” አቶ ኢያሱ ፣ አቶ ታምራት፣ ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴና አትሌት ገዛኦኝ ወልዴ እኛን የመክሰስ መብት ስለሌላቸው ዕግዱ ተነስቷል”
ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
/የኦሎምፒክኮ ሚቴው ፕሬዝዳንት /
- ማሰታውቂያ -
የመደበኛ ፍርድ ቤት የውሳኔና የዕግድ መቀልበስን በማንሳት አጋነን ማውራት ማጯጯህ አይጠቅም ብለን እንጂ ስለ ሂደቱ በደንብ መናገር አቅሙ አለን” ሲሉ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ተናገሩ።
ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቤስት ዌስተርን ፕሪሚየም ሆቴል የኦሎምፒክ ኮሚቴ መግለጫ ላይ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አሸብር እንደገለጹት ” ክሱን የፈጸሙት አራቱ አካላት በቀጥታ የማይመለከታቸው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገልጸናል። በአቶ ኢያሱ የሚመራው የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታግዷል በእኛም በኩል ተቀባይነትና ዕውቅና የለውም በቀጣይ አዲስ የቦክስ ፌዴሬሽን አቋቁመን ህዳር 4 ለሚደረገው አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የልኡካን ቡድንን እናሳውቃለን ለአቶ ታምራትና ለቴኒስ ፌዴሬሽን እውቅና አልሰጠንም ጉባኤ ሲያካሂዱ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አልተጠራም አናውቀውም አቶ ታሞሬት እኛ ጋር እያለ
በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሰም አካውንት ከፍቶ ትጥቅ ሲነግዱ በዲሲፕሊን የተሰናበቱ በመሆናቸው ማንንም በመወከል እኛን የመክሰስ መብት የላቸውም ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ አባላት የሚያነሱትን ጥያቄ ነው የከሰሰን ሃይሌ የጉባኤ አባል አይደለም
አትሌት ገዛኦኝ አበራም አባል አይደለም . ፌዴሬሽናቸው እንጂ አቶ ገዛኧኝ እኛን መክሰስ አይችሉም ደራርቱ ባልወከለችው እኛን የመክስ መብት የለውም በአጠቃላይ የከሰሱን የማይችሉ መሆናቸውን ነግረን ውሳኔውን አስቀልብሰናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር አሸብር አጽንኧት በሰጡት መግለጫቸው “ሚዲያው ተጨፍልቆ ተደባልቆ ከመሳደብ ከመደገፍ ከመተቸት ያዘጋጀነው ሰነዱን አስቀድሞ ማወቅ ነበረበት በሚል ክፍተቱን ወደ እኛ ወስደናል ዕቅዱን ሰነዱን ማወቅ ለመከራከርም ለመተቸትም ሆነ ለመደገፍ ይመቻል” ሲሉ በቀጣይ ምን ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ፕሬዝጃንቱ እንዳሉት “መሸሽ አያስፈልግም ለውጤት መጥፋቱ የጋራ ተጠያቂነት ነው የኛም የሚዲያም ድርሻ አለ ሚዲያው አትሌቱን አሰልጣኙን ጠርቶ ሲሳደብ አዕምሮ ይጎዳል ይህን ክፍተት ሚዲያው እንደራሱ መውሰድ አለበት ” ሲሉ በፓሪስ ኦሎምፒክ ደካማ ውጤት ሚዲያውም ድርሻ አለው ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የ8 አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በቅርቡ ባለድርሻ አካላት ለውይይት እንደሚቀርብ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
የኮሚቴው አመራሮች ዛሬ ጠዋት በሰጡት የቅድሚያ መግለጫ ላይ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አሸብር የመግለጫው ዋና አላማ ኮሚቴው ላይ ስለተሰጠው ዕግድና ዕግዱ ስለመነሳት ሳይሆን ስለ ስትራቴጂክ ፕላንና ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በጋራ እንዴት እንደምንሰራ ለመግለጽ ነው ” ሲሉ በአራት ወገኖች የቀረበባቸው ክስ እንደማያሰጋቸው ያሳዩበትን አስተያየት ሰጥተዋል።
በዚህ የ8 አመት የስትራቴጂክ ፕላን መሰረት ኦሎምፒክ ኮሚቴውን በተደራጀና በተቀላጠፈ መንገድ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል በአዳዲስ ጊዜውን የዋጀ የስትራቴጂ ሰነድ ለባለድርሻ አካላት እንደሚቀርብ ተገልጿል። በተለይ በ ቪ ፒ አር ጥናት የኮሚቴው የኮሚኒኬሽን ዘርፉና የስፖርትን ልማት የሚያጠናክርና ወደተሻለ ስኬት እንዲገባ የሚያደርግ ጥናት እንደሆነ የገለጹት አመራሮቹ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የፓሪስ 2024 ዝርዝር ውጤቶችን በግልጽ የሚያሳይ እያንዳንዱን ተግባርና ሃላፊነት የሚገልጽ የውድድሩ ውጤት ላይ የታየው ጠንካራና ደካማ ጎን ወጥቶ በቀጣይ እንዴት መቀጠል አለበት የሚል ዝርዝር ሪፖርት እንደሚቀርብም ተወስቷል። በዚህ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው የፊታችን ሃሙስ መስከረም 9 ለፓሪስ ኦሎምፒክ የልኡካን አባላት ሽልማትና የዕውቅና ስነስርዓት በማሪዮት ሆቴል እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።
በመግለጫው ላይ ከዶ/ር አሸብር ውጪ ዋና ጸሃፊው አቶ ዳዊት አስፋው ሀቃቤ ነዋይዋ ኤደን አሸናፊና የፓሪስ 2024 የቴክኒክና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ተገኝተዋል።
ከ2013-2020 ድረስ ለቀጣዮቹ 8 አመታት የሚቀርበው
ይሄ ስትራቴጂክ ጥናት በቀጣይ የስፖርቱን ባለድርሻ አካላት የሚያወያይ እንደሚሆን ይጠበቃል።