ብሄራዊ የዳኞች ኮሚቴ ተበተነ

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ስብሰባ የኢትዮዺያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በአቶ ኢብራሂም መሀመድ የተሰባሰቡት ኮሚቴዎች እንዲቀየሩ ተወሰነ።

በፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቢሮ ውስጥ በተካሄደውና ፕሬዝዳንቱ በመሩት ውይይት በአዲስ አበባ በጅማና በባህርዳር ከተማ የተካሄደው የፕሪሚየር ሊጉ ሂደት ላይ ከተወያዩ በኋላ የኮሚቴው አባላቶች በአዲስ እንዲተካ መወሰኑ ታውቋል።

በአቶ ኢብራሂም የሚመራው ኮሚቴ ኢንስትራክተር መኮንን ኢንስትራክተር ፍቃዱ ኢንስትራክተር ሃይለ መላክ ሻለቃ በልሁና ከኮሚቴው ከራቀ የቆየው ኢንስትራክተር ቸርነት የተካተቱበት እንደነበር ይታወቃል። አቶ ኢብራሂም ለቀጣዮቹ ጊዜያት የሚሆኑትን በእጩነት ካቀረበ በኋላ በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከጸደቀ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport