ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ውጤት ለውጠዋል ያላቸውን ሁለት አርቢትሮችን ሲመልስ ምደባ ውስጥ ያልነበረውን አርቢትር ወደ አዲስ አበባ ጠርቷል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቀለ 70 እንደርታ ጋር 1ለ1 በተለያዩበት ጨዋታ በግጥሚያው መጠናቀቃያ አካባቢ መቀለ 70 እንደርታ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ሞት በመከልከሉ ውጤት ለውጧል በሚል ፌዴራል አረቢትር ተፈሪ አለባቸውን ከምደባ ውጪ አድርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ባሸነፈበት ጨዋታ ጎል የሆነው ኳስ ኦፍሳይድ ቢሆንም . ፌዴራል ረዳት አርቢትር ሚፍታ ሁሴን በማጽደቁና ውጤት በመቀየሩ ከምደባ ተሰናብታል።
ይህን ተከትሎ በኮሚቴው ምደባ ውስጥ ያልታሰበውን ተሰናባች ኢንተርናሽናል ዳኛ አሸብር ሰቦቃን መጥራቱ ታውቋል። ይህም ከአምናው ኮከብ ዳኛ ማኑኤ ወ/ጻዲቅ በመቀጠል ከምደባ ውጪ ተደርጎ በችግር የተጠራ ሁለተኛ አርቢትር ሆኗል።
- ማሰታውቂያ -
የኮሚቴው ቁጣና አርጩሜ በፌዴሬሽኑ አመራሮች ቁርጠኛ አቋም ወይስ ኮሚቴው አቋሙን ለውጦ የሚለው እስካሁን የታወቀ ነገር የለም


