“መንግስትና ህዝቡ ድጋፍ ሳያደርጉ ውጤት ይጠብቃሉ ነገር ግን አዳነ ግርማና ሳላህዲን ሰይድን በድጋሚ መፍጠር አልቻልንም””
ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ
/ የኢት. እግርኳስ ፌዴሬሽን ም/ል ፕሬዝዳንት/
” ኢትዮጵያ በ2029 የአፍሪካ ዋኝጫ ስታዘጋጅ ብሄራዊ ቡድኑን ከሚመሩት አሰልጣኞች መሀል እንድትገኙ እመኝላችኋለሁ”
ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
” የፋስት ትራክ ስልጠና ለብዙዎች ጥያቄ ምላሽ የሰጠ በመሆኑ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ”
አቶ ባህሩ ጥላሁን
/የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ/

- ማሰታውቂያ -
” ስልጠናውን የምትወስዱት ሰላሳዎቹ አሰልጣኞች እያንዳንዳችሁ የዛሬ አምስት አመት አንድ ተጨዋች ካወጣችሁ እንደ ደሀገር ለውጥ ይመጣል” ሲሉ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ም/ል ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ30 አሰልጣኞች ያዘጋጀው ፋስት ትራክ የቢ ላይሰንስ ስልጠና ሲጀመር የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንትና የቴክኒክ ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ እንደገለጹት ” ይሄ ስልጠና ትልቅ እድል ነው ፌዴሬሽናችን እናንተን ለማገዝ ዝግጁ ነው ይሄ ፋስት ትራክ በትግል የተገኘ እድል በመሆኑና በመሳካቱ ደስ ብሎኛል በርቱ ከተጨዋችነት ወደ አሰልጣኝነት ስትቀየሩ ማንበብና ጽናት ይጠይቃል” ሲሉ መክረዋል።
ዶክተሮ ዳኛቸው እንደተናገሩት ” የዛሬ አምስት አመት ስልጠና የምትወስዱት ሰላሳዎቹ አሰልጣኞች እያንዳንዳችሁ አንድ ተጨዋች ካወጣችሁ እንደ ሀገር ለውጥ ይመጣል ባለፉት አምስት አመታት አንድ አሰልጣኝ አንድ ተጨዋች ማፍራት አልቻልንም ይህን ማድረግ አቅቶን ነው የተቸገርነው ሲሉ ገልጸዋል።
እንደ ምክትል ፕሬዝዳንቱ “መንግስትና ህዝቡ ድጋፍ ሳያደርጉ ውጤት ይጠብቃሉ ነገር ግን አዳነ ግርማና ሳላህዲን ሰይድን በድጋሚ መፍጠር አልቻልንም ለዚህ ነው እናንተ ላይ ትልቅ አደራ ያለው” ሲሉ ሰልጣኞቹን አበረታተዋል።
የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደተናገሩት የፋስት ትራክ ስልጠና ለብዙዎች ጥያቄ ምላሽ የሰጠ በመሆኑ ሰላሳችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ስልጠናው የግድ በማስፈለጉና ላይሰንስ መያዝ ስላለባችሁ እንጂ የናንተ ልምድ በራሱ በጣም አስፈላጊ ነው ካፍ የፈቀደው ለ25 ሰልጣኞች ቢሆንም ፕሬዝዳንታችን ከካፍ ሰዎች ጋር ተነጋግረው አምስት ኮታ ተጨምሮ ለ30 አሰልጣኞች መፈቀዱ አስደስቶኛል ስኬታማ የስልጠና ጊዜ እኔዲሆን እመኛለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሚሰጠው የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተርነት አብርሃም መብራቱ በበኩሉ ” እናንተን በማሰልጠኔ ደስተኛ ነኝ ወደዚህ ትራክ በመግባታችሁ ደስ ብሎኛል ኢትዮጵያ በ2029 የአፍሪካ ዋኝጫ ስታዘጋጅ ብሄራዊ ቡድኑን ከሚመሩት አሰልጣኞች መሠል እንድትገኙ እመኝላችኋለሁ” ሲል ተናግሯል።
ለስልጠናው ስ ኬት ትልቅ አስተዋጼኦ ያደረጉትን ባለሙያዎች ያመሰገነው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ” ጉልህ ሚና የነነበራቸውን ፕሬዝዳንቱ ኢሳያስ ጅራን አመሰግናለሁ የካፍ የቴክኒክ ዳይሬክተር ከጉዞና ከግል ጥቅም በዘለለ ለልማትና ለስልጠና የሚጥሩ የሁለት ሀገራት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች የሆኑት የኛው ኢሳያስ ጅራና የላይቤሪያ አቻቸው ሙስጠፋ ራጂ ብቻ ናቸው ብሎ አድንቋል” ሲል ሁለቱን ፕሬዝዳንቶች አሞግሷል።
በስልጠናው ከካሳዬ አራጌ እስከ ኤፍሬም ወንደሰን፣
ከአዳነ ግርማ እስከ ሳላህዲን ሰይድ ፣ ከደጉ ደበበ እስከ ሳምሶን ሙሉጌታ፣ ከዳዊት እስጢፋኖስ እስከ ፍጹም ገ/ማሪያም ፣ ከአስራት መገርሳ እስከ አበባው ቡጣቆ ፣ ከራውዳ አሊ እስከ ኤልመዲን መሃመድ ድረስ በስልጠናው ተሳታፊ ናቸው።
ይሄ ስልጠና በአፍሪካ ደረጃ ከሞሮኮ ቀጥሎ የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።


