ከጸደቀው የክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ ውጪ የሆነ አሰራርን ተከትሎ ዝውውር ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ዘጠኝ ተጨዋቾች በፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ለጥያቄ መጠራታቸው ተሰማ።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ እስከ ትላንት ድረስ ከተደረጉና ከጸደቁት ዝውውሮች በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጸድቀው ይፋ ሲደረጉ አልቀበልም ብለው የሄዱት ገንዘብና አሁን በጸደቀው ውል ፈረሙ የተባለበት ገንዘብ በመቶ እና በሁለት መቶ ሺዎች ቀንሶ መሆኑ በርካታ የስፖርት ቤተሰብን ግራ ሲያጋባ ሰንብቷል።
የኡትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ዝምታ ያሳሰባቸው ወገኖችም ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። አምስት አባላት ያሉት የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ውስጥ ውስጡን እየሰራ መሆኑና ሊግ ካምፓኒው ህገወጦችን እንደማይምር ክለቦችና ተጨዋቾች ከህገወጥ ተግባራቸው
እንዲጠነቀቁ የኮሚቴው ጥርስ የሰላና የማይምር መሆኑን የአክሲዮን ማህበሩ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ከቀናቶች በፊት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ዛሬ ከቀትር በኋላ በተገኘ መረጃ ከተለያዩ ወገኖች ከቀረቡለት መረጃዎችና የመርማሪው ኮሚቴ ዝውውራቸው አጠራጥሮኛል ያላቸውን ዘጠኝ ተጨዋቾችን ወሎ ሰፈር በሚገኘው የአክሲዮን ሜህበሩ ጽ/ቤት በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ እንዲገኙ ለጥያቄ መጥራቱ ታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
የመረጃ ምንጩ የተጨዋቾቹን ማንነት ለጊዜውም ቢሆን ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል።