ሀፊዝ ኮንኮኒ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሁለት አመት ስምምነት ፈርሟል
ሀፊዝ ኮንኮኒ ባሳለፍነው አመት በጋና ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢና ኮከብ ተጫዋች ነበር።
ኮንኮኒ አማጃንዴ በሚባል ቡድን ዝቅተኛ ሊግ ላይ ነበር የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው እናም ቡድኑን ወደ ጋና አንደኛ ሊግ አሳደገ በመቀጠል አዲስ ወደ ጋና ፕሪሚየር ሊግ ወዳ አደገው ቦሎኛ ስታርስ ተቀላቀለ ሰምንት ግዜ ተሰልፎ ሁለት ጎል አስቆጥሯል ። በመቀጠልም ለቤካሀም ዩናይትድ በመፈረም በነሀሴ ወር በስድስት ጨዋታ አምስት ጎል በማስቆጠር የወሩ ምርጥ ተጫዋቾች እጩ ለመሆን በቃ።
አሁን ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከመምጣቱ በፊት በታንዛኒያ ከያንግ አፍሪካንስ ይጫወት ነበር