መነሻ ገጽ ዜናዎች አቶ አሊሚራህ መሀመድና አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከምርጫ ውጪ ሆኑ
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ አሊሚራህ መሀመድና አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከምርጫ ውጪ ሆኑ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስመራጭ ኮሚቴ ከተወሰነ ደቂቃዎች በኋላ ይፋ በሚያደርገው የተወዳዳሪ ዕጩዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የአቶ አሊሚራ መሀመድና የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ ስም እንደማይኖር ተረጋገጠ።

ከፌዴሬሽኑ ታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ በአቶ ሳህሉ ገ/ወልድ፣ በአቶ ጁነዲን ባሻና በአቶ ኢሳያስ ጅራ የፕሬዝዳንትነት ዘመን ባለፉት 12 አመታት በስራ አስፈጻሚነት የሰሩት የአፋሩ አሊሚራህ መሀመድ ከምርጫ ውጪ ሆነዋል። ኮሚቴው በተከታታይ ሶስት አመት ይሁን በተለያየ ጊዜ የሰራ አይካተትም በሚለው አቶ አሊሚራህን ከውድድሩ ውጪ አድርጓል።

ኮሚቴው በተጨማሪ የሀረሪ ክልል ለአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የሰጠውን ውክልና ማንሳቱን ተቀብሎ አቶ ገዛኸኝን ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጪ አድርጓቸዋል። አቶ ገዛኸኝ ክልሉ ውክልናዬን ማንሳት አይችልም ቢሉም ኮሚቴው በተቀመጠው ህግ ክልሉ ውሳኔውን የመሻር መብት አለው ብሎ የአቶ ገዛኸኝ ውክልናን ውድቅ አድርጎታል።

ሁለቱም ዕጩዎች ከዛሬ ጀምሮ በአቶ አንበሳው እንየውና በአቶ ብርሀኑ ከበደ ለሚመራው ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ የመጠየቅ መብት አላቸውም ተብሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...