👉…እስከ ነሀሴ 6 በስራ ላይ ይሆናል
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ስራውን እንደሚጀምር ይጠበቃል።
በፌዴሬሽኑ የህግ አማካሪ በአቶ ሃይሉ ሞላ የሚመራው የአስመራጭ ኮሚቴ 26 ለስራ አስፈጻሚ 3 ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ይፋ በማድረግ ስራውን ትላንት በይፋ ጨርሷል።
በአስመራጭ ኮሚቴው መብቱ የተነፈጋቸው የሀረሪ ክልል ውክልና ያነሳባቸው አቶ ገዛኸኝ ወልዴ፣ ለሶስት የምርጫ ዘመን ተወዳድረው ለአራተኛ ጊዜ ህጉ የከለከላቸው የአፋሩ አቶ አሊሚራህ መሀመድ፣ በህጉ መሠረት በአምስት ክለቦች ያልተደገፈ መረጃ አምጥተዋል የተባሉት ሶስቱም የጋምቤላ ክልል ዕጩዎችና ሙሉ መመዘኛ አሟልቶ ባለማቅረብ እንደ ክልል የቢኒሻንጉል ጉሙዝ ከምርጫ ውጪ በመደረጋቸው ሶስት አባላት ላሉት የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ከዛሬ ሀምሌ 27-ነሀሴ 6 /2014 ድረስ ይግባኝ የመጠየቅ ዕድል ተሰጥቷቸዋል።
የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሶስቱ አባላት ደግሞ የብሄራዊ
የስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንበሳው እንየው…በቀድሞ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ ዘመን ም/ል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ
ብርሀኑ ከበደና የወወክማ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መኮንን ጤናው መሆናቸው ታውቋል።

አስተያየት ይስጡ