*... የፋይናንስ ሃላፊው በፀጥታ ሃይሎች ተያዘ
ሀድያ ሆሳእና ከ15 ተጨዋቾች ጋር ተያይዞ የፌዴሬሽኑ የፍትህ አካላት ውሳኔን ተግባራዊ ባለማድረጉ ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳያገኝ ታገደ።
የክለቡ አመራሮች አዲሱን አሰልጣኝና ተጨዋቾች ፊርማ ለማስፈረም ፌዴሬሽን ቢሄዱም የ15 ተጨዋቾቹን ደመወዝ ካልፈለገ አዲሱን ውል ማጸደቅ እንደማይችል ተነግሯቸዋል።
ያምሆኖ የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ “ተጨዋቾቹ ጋር ያለንን ንብረት መቀበል አለብን ከዚያ በኋላ ነው ስለክፍያው የምናወራው እገዳውን በተመለከተ ግን መረጃው አልደረሰንም” በማለት ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በደረቅ ቼክ ላይ ፈርመዋል የተባሉት የፋይናንስ ሃላፊው በፖሊስ መያዛቸውን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።
የፋይናንስ ሃላፊውና ስራ አስኪያጁ ደረቅ ቼክ ላይ በመፈረማቸው በፖሊስ የሚፈለጉ ሲሆን እስካሁን ስራ አስኪያጁ አለመያዛቸው ታውቋል።