ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ ከክፍያ ጋር ተያይዞ ድርድር ላይ የነበረው አስቻለሁ ታመነና ኦኪኪ አፎላቢን በይፋ አስፈርመዋል።
የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ፋሲል ከነማ ራሱን እያጠናከረ ሲሆን የቅድሚያ ክፍያው በቼክ ይሁን በካሽ በሚል ሲደራደሩ የቆዩትን የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ የኋላ ደጀን አስቻለሁ ታመነን ለማስፈረም ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ደርሰው እየተፈራረሙ ነው ።
ፋሲል የቀጣዩ አመት ባለድል ለመሆንና ሁለተኛው የተከታታይ አመታት ሻምፒዮን ለመሆን ራሱን እያጠናከረ ስብስቡን ጋላቲኮ እያደረገ ነው።
ፋሲሎች ከ5 አመታት የገብረ መድህንና ኦኪኪ ጥምረትን በማፍረስ ኦኪኪ አፎላቢን ለማስፈረም ተስማምተዋል። ተጨዋቹ ከሀገሩ ሲመጣ ፊርማውን የሚያኖር ሲሆን ከአራት አመታት የጅማ አባጅፋርና መቀለ 70 እንደርታ ቆይታና ከ2 ተከታታይ አመታት የሊጉ ድል በመለስ ከአምናው ሲዳማ ቡናን ከመውረድ የማትረፍ ዘመቻ በኋላ ኦኪኪ ከአሰልጣኝ ገብረ መድህን ጥላ ውስጥ መውጣቱ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ