👉 ለጭማሪው የኢኮኖሚ ጫናው
ምክንያት ሆኗል…
ከዋሊያዎቹ ጋር ወደ ካሜሩን ከሚጓዙ 500 ደጋፊዎች መሃል ለመሆን በርካታ ደጋፊዎች እየተመዘገቡ መሆናቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ይህን ምዝገባ እያከናወነ ሲሆን ቁጥራቸውበርካታ የስፖርት ቤተሰብ እየተመዘገበ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምዝገባው ሊጠናቀቅ እንደሚችል ገልጸዋል።
ከጃንዋሪ 9//2022 እስከ ፌብሩዋሪ 6/2022 በካሜሩን ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ከስምንት አመታት ቆይታ በኋላ የተመለሱትን ዋሊያዎቹን ለመደገፍና የኢትዮጵያን መልካም ስም ለመላው አለም ለማሳየት አጀንዳ ያለው ይኸው ጉዞ በስኬት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል። ለ10ቀናት ቀሚኖረው ቆይታ ሙሉ ወጪያቸው ተችሎ ከሚሄዱት 25 ጋዜጠኞች ውጪ ሌሎች የአውሮፕላን የምግብና የማረፊያ ፣ በካሜሩን ቆይታ ለሚንቀሳቀሱበት የመኪናና የስታዲየም መግቢያ ወጪን ችሎ 68 ሺህ 223 ብር እንደሚከፈል ታውቋል።
አዘጋጅ አካሉ እንደገለጸው አስቀድሞ ይፋ ተደርጎ በነበረው የ55 ሺህ 223 ብር ክፍያ ላይ ጭማሪ የተደረገው በተፈጠረው ከሰሞኑ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ጫና ምክንያት ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ነው።
ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽንም አስቀድመው ተመዝግበው የነበሩት ደጋፊዎችን ቢሮ ድረስ በመጥራትና ሁኔታውን በማስረዳት መግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በአስገዳጅ ምክንያት በተሻሻለው 68ሺህ 223 ብር ምዝገባው እንደሚቀጥል ታውቋል
አስተያየት ይስጡ