መነሻ ገጽ ሴካፋ የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገራት ከ23 ዓመት በታች ውድድር አዘጋጅ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
ሴካፋዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ሀገራት ከ23 ዓመት በታች ውድድር አዘጋጅ ብሔራዊ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡

አጋራ
አጋራ

በባህር ዳር ከተማ ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ውድድር በፌዴሬሽኑ የተቋቋመው የሴካፋ ብሔራዊ ውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ዛሬ ሐምሌ 1/11/2013 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጠ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ.እና የፌዴሬሽኑ ም/ ዋና ፀሐፊ እና የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ሰሎሞን ገ/ሥላሴ መግለጫውን ሰጥተዋል።

በመግለጫው ውድድሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአማራ ክልል ጋር በመቀናጀት በማዘጋጀቱ የአገሪቷ ወጣቶች በእግር ኳስ ተሳትፎ በማግፕታቸው በእግር ኳሱ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የአገራችንን ገጽታ ለመገንባት ትልቅ እድል ይፈጥራል።

ለእዚህም የውድድር ኮሚቴው በቅድመ ውድድር ፕሮግራሙ ኮሚቴዎችን ከባህር ዳርና ከፌዴሬሽኑ በተውጣጡ አባላት በማዋቀር ወደ ስራ በመግባት ለውድድር አስፈላጊ የሆኑ የውድድርና የልምምድ ሜዳዎች፣ የኮቪድ 19 እና ዶፒንግ፣ የፀጥታ፣ መስተንግዶ እና አቀባበል እንዲሁም መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ እየተሰራ እንደሆነ፣

ውድድሩ ከሐምሌ 10 እስከ 25/2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ እና ተሳታፊ የሆኑት 11 የሴካፋ አባል አገራት ከሐምሌ 7 ቀን 2013 ጀምሮ ወደ ባህርዳር እንደሚገቡ እና የኮሚቴው አባላትም በተቀናጀ መልኩ በባህር ዳር ውድድሩን በድምቀት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ፣

በመጨረሻም በኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት የባህር ዳር ስታዲየም ከሚይዘው የተመልካች ብዛት አንድ አራተኛ (ሃያ አምስት ሺህ ) ተመልካች እንደተፈቀደና በኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት እንደሚስተናገድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ ገልፀው ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...