በ ዛሬው ዕለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያደረገው የኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ቡድን ለሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረቡ ለማወቅ ተችሏል ።
የኢትዮጵያ ቡናው አስራት ቱንጆ እና የኢትዮጵያ መድህን ግብ ጠባቂው ታምራት ዳኜ ከ ነገ ጀምሮ ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምድ መስራት ይጀምራሉ ።
አስራት ቱንጆ በዛሬው እለት ብሔራዊ ቡድን ያደረገውን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በመድህን ሜዳ በመገኘት ታድሟል ።
ከ ዛሬው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በኋላ ፀጋሰው ዴማሞ እና አማኑኤል እንዳለ ከዚህ በተጨማሪም ሀይለ ሚካኤል አደፍርስ በ ” ህመም ምክንያት ” መቀነሳቸው ለማረጋገጥ ችለናል ።
በጣም ጥሩ ነው ጎበዝ ጀግኖቻችን በርቱልን ። ሌላው ይህ ኢንፎርሜሽንን በጎግል ድረ ገፅ በማግኘቴ በጣም ተደስቻለሁ ያውም በራሴ ቛንቛ, “To be honest, I am fed up with these foreign language ” that doesn’t mean neither I don’t speak nor understand it. በዚህ የተነሳ እሜል አደራሻዬንም ሆነ ማንኛውንም ነገር እሰጣችሁአለው የአላችሁን ዜናም ሆነ ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ለማግኘት ዝግጁ ነኝ
Best top information site
So I like this page