ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንም ያልፈየዱ ሦስት የውጪ ዜጋ ሴት ተጫዋቾች ተሰናበቱ።
በኢትዮጵያ የሴት እግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአንድ አመት ለመጫወት ፈርመው የነበሩት እና በሴካፋ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ እና በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ከእኛ ሀገር ተጫዋቾች የተለየ ነገር ማሳየት ያልቻሉት የከፍተኛ ዶላር ተከፋይ የነበሩት የናይጄሪያ ሊግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ በ15 ግቦች ሆና የመጣችው አጥቂዋ ቦላዲ ኦላሚንዴ ፣ ግብ ጠባቂ ፌይዝ ኦሚላና ተከላካዩዋ ኦፔይሚ ሳንደይ ንግድ ባንክን በተለየ መጥቀም ሳይችሉ አንድ አመት ሳይሞላቸው ሦስቱን ናይጄሪያዊያን ከክለቡ ተለያይተዋል።


